በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግሎባላይዜሽንና “አሜሪካ ትቅደም” በዓለም መድረክ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በስዊትዘርላንዷ መዝናኛ ከተማ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ለመሣተፍ እንደደረሱ። Davos, Switzerland January 25, 2018.
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በስዊትዘርላንዷ መዝናኛ ከተማ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ለመሣተፍ እንደደረሱ። Davos, Switzerland January 25, 2018.

ላለፉት 18 ዓመታት አንድ ሥራ ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ሲሣተፍ የአሁኑ የመጀመሪያው ሊሆን ነው።

የስዊስ ፖሊስ ዳቮስ ጥበቃ ላይ
የስዊስ ፖሊስ ዳቮስ ጥበቃ ላይ

“አሜሪካ ትቅደም” የሚለውን አጀንዳቸውን ያብራሩበታል በተባለ ጉዞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በስዊትዘርላንዷ መዝናኛ ከተማ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም ምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ እየተሣተፉ ናቸው።

የሚስተር ትረምፕ ፖሊሲ ዓለምአቀፍ የንግድ ስምምነቶችና ውሎች እንደገና እንዲፈተሹ ወይም ለድርድር እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሲሆን ዋሺንግተንም በአንዳንድ ገቢ ሸቀጦች ላይ አዳዲስ ታሪፎችን እንድትጥል አድርጓታል።

የዳቮስ መድረክ ተሣታፊዎች ዛሬ በዓለም ውስጥ እየታዩ ያሉ የአመለካከት ግጭቶችን ማስተናገድ ይኖርበታል እየተባለ ነው።

ይህ ዓመታዊ የዓለም ምጣኔ ኃብት መድረክ ለዓለም የፖለቲካና የንግድ መሪዎች “ሊታይ የሚገባው ቦታ ነው” ነው የሚባለው።

የዘንድሮው የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ አንድ ልብ አንጠልጣይ ተሣትፎ ጨምሯል። ላለፉት 18 ዓመታት አንድ ሥራ ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሲሣተፍበት የአሁኑ የመጀመሪያው ሊሆን ነው። በጉባዔው ላይ የተገኙ የመጨረሸው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ነበሩ - በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም.

ተስፋቸው የነቃ እንደሆነ የሚታይባቸው የዓለም ምጣኔ ኃብት መድረክ ፕሬዚዳንት ቦርዥ ብሬንድ በመነጋገር አጥብቀው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። እዚያ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትም የተሻለ መተካከል ባለበት ዓለምአቀፋዊ ሥርዓት፣ ግሎባላይዜሽን ላይ ውይይት ይከፍታሉ ብለው እንደሚጠብቁ አመልክተዋል።

እነዚህ የማስፈፀሚያ ትዕዞዞች የፍትኀዊ ንግድን መርኆች የሚያጠናክሩና ከእንግዲህ አሜሪካ ጥቅም ሊመታባት የሚቻል ሃገር አለመሆኗን የሚያሳዩ ናቸው።
ዶናልድ ትረምፕ - የዩናይትድ ሰቴትስ ፕሬዚዳንት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የዳቮሱን ጉባዔ ነገ፤ ዓርብ በንግግር ይዘጋሉ። ከዚያ በፊት የተነሣው ውጥረት ግን የእርሣቸው ግሎባላይዜሽን እና ተያይዞም ነፃ የግብይት ሥርዓት ወይም ግንኙነቶች ላይ ያላቸው ነጭናጫ የሚባል ጠባይ ነው።

አሁን እየተሠራበት ያለው የንግድ አያያዝ ‘አሜሪካን የሚጠቅም አይደለም’ ብለው የሚያምኑት ሚስተር ትረምፕ ከዋጭ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገቡ የልብስ ማጠቢያ መኪኖችና በፀሐይ ኃይል ሰብሳቢ ኤሌክትሮኒክ ጣውላዎች ወይም ሶላር ፓነልስ ላይ ከፍ ያለ የቀረጥ ጭማሪ የሚያሳድር ትዕዛዝ ትናንት ወደ ዳቮስ ከመውረዳቸው በፊት ፈርመዋል።

“እነዚህ የማስፈፀሚያ ትዕዞዞች - አሉ ትረምፕ ፕሬዚዳንታዊ ፊርማቸውን ሠነዱ ላይ ከማስፈራቸው በፊት ሲናገሩ - የፍትኀዊ ንግድን መርኆች የሚያጠናክሩና ከእንግዲህ አሜሪካ ጥቅም ሊመታባት የሚቻል ሃገር አለመሆኗን የሚያሳዩ ናቸው።”

ጉባዔው ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ሲጀመር የመክፈቻውን ንግግር ያደረጉት የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ያስተላለፉት መልዕክት ከአሜሪካዋ መሪ የአስተሳሰብ ዋልታ ጋር ፊት ለፊት የሚጋጭ ነው።

የራሣችንን የራሣችንን የሚሉ ኃይሎች በዓለምአቀፉ የንግድ ልውውጥ ሥርዓት (ግሎባላይዜሽን)ላይ እየተነሡበት ነው፤ ሃሣባቸው እነርሱ ራሣቸው ግሎባላይዜሽንን ወደጎን መግፋት ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ፍሰቱንም የመቀልበስ ነው።
ናሬንድራ ሞዲ፤ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር

“የራሣችንን የራሣችንን የሚሉ ኃይሎች በዓለምአቀፉ የንግድ ልውውጥ ሥርዓት (ግሎባላይዜሽን) ላይ እየተነሡበት ነው - ብለዋል ሞዲ። “ሃሣባቸው - አሉ ሞዲ በመቀጠል ‑ እነርሱ ራሣቸው ግሎባላይዜሽንን ወደጎን መግፋት ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ፍሰቱንም የመቀልበስ ነው።”

ይህንን የሞዲን አስተሳሰብ ዳቮስ ላይ የታደሙ ወትሮ የአሜሪካ ወዳጅና አጋር የሆኑ የአውሮፓ ሃገሮችን መሪዎች ጨምሮ ቻይናና ጃፓንንም የመሳሰሉ ግዙፍ ምጣኔ ኃብቶች ይጋሩታል።

ትረምፕ ይዘውት የተጓዙትን ሃሣብ ዳቮስ ላይ ብዙዎች ማዳመጥ፣ መስማትም አይፈልጉ ይሆናል እየተባለ ነው።

ግሎባላይዜሽንና “አሜሪካ ትቅደም” በዓለም መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00
ግሎባላይዜሽንና “አሜሪካ ትቅደም” በዓለም መድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG