በኦሞ ወንዝ መሙላት ምክንያት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ዳሰነች ወረዳ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች በወባ ወረርሽኝ እየተጠቁ መሆኑን፣ የአካባቢው አስተዳደር አስታውቋል።
ወረርሽኙ የተከሰተው በጎርፍ አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ ከ79 ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች በተጠለሉባቸው መጠለያዎች መሆኑንም አመልክቷል ።
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጸው፣ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺሕ 3 መቶ በላይ ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል።
በሽታው በተለይም በእናቶችና ህፃናት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን፣ የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም