በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዳግስታን ከእስራኤል የተነሣ አውሮፕላን ተጓዦች ላይ ተቃውሞ ተደረገ


የዳግስታ አየር ማረፊያ ሩሲያ
የዳግስታ አየር ማረፊያ ሩሲያ

አንድ ከእስራኤል የተነሣ አውሮፕላን፣ በሩሲያው የዳግስታን አየር ማረፊያ እንደደረሰ፣ በመቶ በሚቆጠሩና ፀረ አይሁድ መፈክር በሚያሰሙ ሰዎች ተከቧል።

ተቃዋሚዎቹ፣ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው ሜዳ ዘልቀው በመግባት፣ አውሮፕላኑን ከበው እንደነበር፣ የሩሲያው የዜና አገልግሎት አስረድቷል።

የእስልምና እምነት ተከታዮች በሚበዙባት ዳግስታን በተደረገው በዚኽ ተቃውሞ፣ ከ20 በላይ ሰዎች እንደተጎዱና ሁለቱ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ተቃዋሚዎቹ፣ እስራኤላውያኑን ለመለየት፣ የመንገደኞቹን ፓስፖርት ሲመለከቱ እንደነበር ተዘግቧል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ቪዲዮዎች፣ ሰልፈኞቹ የፍልስጥኤምን ባንዴራ ሲያውለበልቡና የፖሊስ መኪናን ለመገልበጥ ሲሞክሩ አሳይተዋል።

አውሮፕላኑ፣ “ሬድ ዊንግስ” የተሰኘ የሩሲያ አየር መንገድ ንብረት እንደኾነ ታውቋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቢሮ፣ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ የሩሲያ የጸጥታ ኃይሎች፣ የእስራኤል ዜጎች እና አይሁዳውያን፣ ራሳቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ ጥሪ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG