በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ከሁለት ወራት በላይ ለኾነ ጊዜ የታሰሩት አምስትኤርትራውያን ስደተኞች ለማስፈታት እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር ድረስ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።
የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ እስረኞቹ እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ገልጸው፣ “ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች እየደወሉ፣ ለእያንዳንዳቸው እስከ 100 ሺህ ብር ድረስ ክፈሉ ይሉናል” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት በበኩሉ፣ “እስረኞቹ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ግን ግፊት እያደረግኩ ነው” ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም