በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞዛምቢክን በመታው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ የሟቾች ቁጥር ጨምሯል


Cyclone Idai Death Toll Rises as More Bodies Found
Cyclone Idai Death Toll Rises as More Bodies Found

ሳይክሎን ኢዳይ በመባል በሚጠራው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በተመታችው ሞዛምቢክ በገባው የኮሌራ በሽታ፣ እስከ ትናንት ሐሙስ ባለው አኃዝ፣ የሟቾች ቁጥር ከ5 ወደ 139 ማደጉ ተገለፀ።

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/በዚህ ሳምንት መጀመራ ላይ፣ 9መቶ ሺህ በአፍ የሚወሰድ የክትባት ጠብታ፣ ለአካባቢው እንደሚያደርስ ማስታወቁ አይዘነጋም።

በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ፀረ ኮሌራ ዘመቻ በየመገናኛ ብዙኃኑና በየአደባባዩ በሚገኙ ድምፅ ማጉያዎች እየተካሄደ መሆኑን፣ የፈረንሳዩ ዜና አውታር ዘግቧል።

በሽታውን ጨርሶ ለማጥፋት ያለው ዕድል የተመናመነ እንደሆነ ነው ዩኒሴፍ እየገለጸ ያለው።

ሞዛምቢክን የመታው፣ ኃይለኛ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ፣ ማላዊንና ዚምባብዌንም አጥቅቷል፡፡

የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶኒዎ ጉቴሬዥ፣ በሳይክሎን ኢዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ሦስት የደቡባዊ አፍሪካ ሀገሮች፣ “ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በአስቸኳይ ሊደርስላቸው ይገባል” ሲሉ ማክሰኞ ዕለት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG