በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሳይክሎን ፋኒ" ማዕበል ምሥራቃዊ ህንድን እየደበደበ ነው


"ሳይክሎን ፋኒ" ማዕበል ምሥራቅ ህንድ ግዛት ደርሶ በከባድ ዝናብና ንፋስ አካባቢውን እየደበደበ ነው።

“ኦዴሻ” በሚባለው የህንድ ግዛት የደረሰው ዛሬ ማለዳ ሲሆን፣ ማዕበሉ የሚያልፍበት አካባቢ ቁጥሩ ወደ አንድ ሚሊዮ የሚጠጋ ህዝብ የሚኖርበት መሆኑ ተመልክቷል።

በረባዳ ሥፍራዎች የሚኖረው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የመንግሥቱን ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ለቆ ወጥቷል።

“በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎችን ልናስወጣ አቅደናል” ሲል የመንግሥት ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ትሮፒካል ስቶርም ሪስክ የተባለው የውቂያኖስ ማዕበል ተከታታይ ድርጅት እንዳስታወቀ ሳይክሎን ፋኒ እጅግ የከፋ ከሚባለው ማዕበል በአንድ ደረጃ ብቻ ዝቅ የሚል ሲሆን መጠነ ሰፊ ውድመት ሊያደርስ እንደሚችል አስግቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG