በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወሲባዊ ትንኮሳ እና ስም ማጥፋት የተወነጀሉት ትረምፕ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ጠበቃቸው ተናገሩ


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

ባንድ ወቅት የ “ኤል” መጽሔት ዓምደኛ በነበረችው ጋዜጠኛ ኢ ጂን ኬሮል ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ እና የስም ማጥፋት አድራጎት በመፈጸም፤ ከሕዝብ በተውጣጡ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች የጥፋተኝነት ውሳኔ የተወሰነባቸው የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠበቆች የይግባኝ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ አስታወቁ፡፡

በኒው ዮርክ ፊዴራል ፍርድ ቤት የተሰየሙት ከሕዝብ የተውጣጡት ዳኞች “በቀድሞው ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስገድዶ የመድፈር አድራጎት ተፈጽሞብኛል” የሚለውን የኢ ጂን ኬሮልን ክስ ውድቅ በማድረግ፤ በአስገድዶ መድፈር ደረጃ ከባድ ባልሆነ ሌላ ወሲባዊ ትንኮሳ እና ስም የማጉደፍ አድራጎት ተጠያቂ አድርጓቸዋል። በመሆኑም የአምስት ሚሊዮን ዶላር የጉዳት ካሳ እንዲከፍሉም ወስነውባቸዋል፡፡

ከሳሽ ኢ ጂን ኬሮል ከፍርድ ቤቱ ስትወጣ አንዲት ሴት ጮክ ብላ “በጣም ጎበዝ እና ቆንጆ ሴት ነሽ!” ስትላት “አመሰግናለሁ! አመሰግናለሁ!” ብላ መልስ ከመስጠት ሌላ ለጋዜጠኞች መልስ ሳትሰጥ ሄዳለች፡፡ ትረምፕ በበኩላቸው ውሳኔውን “የተከፈተብኝ የማሳደድ ዘመቻ” በማለት አጣጥለውታል፡፡

በሚቀጥለው ዓመት ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት የተሸነፉበትን ያለፈውን ምርጫ ውጤቶች ለመቀበልበስ ካደረጉት ሙከራ እና የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ የመንግሥት ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሳያስረክቡ ወደፍሎሪዳ ማሮላጎ ይዘው ከመሄዳቸው ጋር የተያያዙ በርካታ ምርመራዎች ተክፍተውባቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG