በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኩባ ስለተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ


ፎቶ ፋይል:-የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጌል ዳያዜል ካኔል
ፎቶ ፋይል:-የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጌል ዳያዜል ካኔል

የኩባው ፕሬዚዳንት፣ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ተቀይሮ፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እንዲፀድቅ መፈለጋቸው ተነገረ።

የኩባው ፕሬዚዳንት፣ የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ተቀይሮ፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እንዲፀድቅ መፈለጋቸው ተነገረ። ሚጌል ዳያዜል ካኔል ትናንት ቬኔዙዌላ ውስጥ ከሚገኘው ጠለሱር ቴኬቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን መፍቀድ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ አድልዎና ልዩነቶችን ሊያስወግድ የሚችል መፍትሔ መሆኑን ተናግረዋል።

የኩባ የእስካዛሬው ህገ መንግሥት፣ ወንድና ሴት በፈቃደኛነት የሚፈጽሙት አንድነት መሆኑን ነው የሚደነግገው። በቀጣዩ ዓመት ይጸድቃል በተባለው አዲሱ ህገ መንግሥት ውስጥ፣ "ጋብቻ" ማለት በሁለት ሰዎች መካከል የሚፈጸም ሕብረት እንደሆነ ይደነግጋል ነው የተባለው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG