በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኩባ ኮቪድ ክትባት


ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

ኩባ በዓለም የጤና ድርጅት እውቅና ያልተሰጠው እና በሃገሪቱ የሚመረት የኮቪድ-19 ክትባትን ከ2 ዓመት እድሜ ጀመሮ ለሚገኙ ሕጻናት መስጠት መጀመሯን ሰኞ ዕለት አስታወቀች፡፡

በሃገሪቱ መንግሥት ሚዲያ ላይም 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝቧን ለማስከተብም ቅስቀሳ እያደረገች ነው፡፡ የመንግሥት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግማሽ የሚሆኑት የሃገሪቱ ዜጎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱ ሲሆን አንድ ሶስተኛዎቹ ደግሞ ሁለቱንም ዙር ክትባት ተከትበዋል፡፡ ባለፉት ሰባት ቀናትም በአማካኝ 7000 ሰዎች በኩባ በየቀኑ በቫይረሱ መያዛቸውን የጆንስ ሆፕኪንስ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ጠቁሟል፡፡

ሃገሪቱ ይህን የምታደርገው ሕጻናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ስትል ነው፡፡ እኤአ ከ2020 መጋቢት ወር አንስቶ በኩባ ሕጻናት ትምህርት በቴሌቪዥኝ እየተከታሉ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በሮም ባደረጉት ንግግር “በወረርሽኙ እንዳየነው ማንኛውም ሃገር ቁጥጥሩን መተው የለበትም መዘናጋት ልክ እንደ ቫይረሱ ጎጂ ነው ስለዚህ መጠቀቅ አለብን" ሲሉ ያሳሰቡ ሲሆን የክትባት ፍትሃዊነት እንዲኖር እና ዓለምን ከወረሽኝ ለመከላከል ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት ላይ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG