በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኩባው ተቃውሞ አንድ ሰው ሲሞት ከ100 በላይ ቆስለዋል


በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና በሚገኘው የምክር ቤት ህንጻ ፊት ለፊት የተካሄደ ተቃውሞ እ.ኤ.አ ሐምሌ 11 2021
በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና በሚገኘው የምክር ቤት ህንጻ ፊት ለፊት የተካሄደ ተቃውሞ እ.ኤ.አ ሐምሌ 11 2021

የኩባ መንግሥት ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ ውስጥ በተነሳው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ አንድ ሰው መሞቱን ሲገልጽ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ ባለሥልጣናቱ ከ100 በላይ ሰዎችን ማሰራቸውን አስታውቀዋል፡፡ መንግሥት የ36 ዓመቱ ሰው የተገደለው ባለፈው ሰኞ ከሀቫና ወጣ ብላ በምትገኘው በአሮዮ ናራንጆ ከተማ በተቃዋሚዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግብግብ መሆኑን አመልክቷል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ትልቅ ተቃውሞ በኩባ ላለፉት አስርት ዓመታት አልታየም፡፡ የተቃውሞ አመጹ ዋና ከተማዪቱን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከተካሄደ ሁለት ቀን በኋላ የኩባ ዋና ከተማ ሃቫና፣ ትናንት ማክሰኞ በከባድ የፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆና ውላለች፡፡

መንግሥትን በመቃወም የወጡት ኩባውያን በምግብ አቅርቦት እጥረት፣ እየናረ በመጣው የዋጋ ውድነት፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና መንግሥት ለኮረና ቫይረሰ በሰጠው ምላሽ እጅግ የተበሳጩ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በኩባው ተቃውሞ አንድ ሰው ሲሞት ከ100 በላይ ቆስለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:06 0:00

የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሮድሪጌዝ ለዚህ ምክንያቱ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች የሚያደርጉት ዘመቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው እሁድ በተለይ በሃቫና ዋና ከተማ የተደረገውን ትልቅ ጸረ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፉን ጨምሮ በየትናንሽ ከተሞች የተካሄዱት ሰልፎች በ እነዚህ ወገኖች የተቀሰቀሱ ናቸው በማለት እንዲህ ይላሉ፡፡

“እነዚህ ፣ “ወቅታዊ ጉዳይ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱት፣ ከአገሪቱ ጋር ምንም ትስስር በሌላቸው፣ ከሰሜን አሜሪካ ግዛት እኩይ ዓላማ ባላቸው ወገኖች ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ፣ የፍሎሪዳ ዲጂታል ሚዲያ፣ አክቲቪስቶችና በቴክኖሎጂ የተቀነባበሩ ዘመቻዎች ውጤታ ናቸው፡፡ ሆን ተብሎ እጅግ ውድ በሆኑ ዘዴዎችና መሳሪዎች በመጠቀም፣ ውዥንብሩን ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ለማድረግ፣ የሚደረጉ ሙከራዎች ሲሆኑ ይህ ድርጊት በአጠቃላይ፣ ጭካኔና ጥሰት የተሞላበት የቲዩተርን የማህብረሰብ ፖሊሲዎች የጣሰ፣ የድርጅቱን ህግ ደንብ ያላከበረ ድርጊት ነው፡፡

የቀድሞ መሪ ራኡል ካስትሮ ባላፈው እሁድ ከፕሬዚዳንት ሚጉ ኤል ዲያዝ ካኔል እና ከሌሎች የኮሙዪኒስት ፓርት አባላት አመራሮች ጋር ተቃዋሚዎችን በሚመለከት ተገናኝተው የመከሩ መሆኑን የኩባ መንግሥት ሚዲያ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም የዩናይትድ ስቴት የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አሌጃንድሮ ሜዮርካስ ይህን ሁኔታ ተከትሎ የኩባ ዜጎች ከደሴቲቱ አገር ከኩባ በመሸሽ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር ለመሰደድ፣ አደገኛ የሆነውን የጀልባ ጉዞ እንዳይሞክሩት አስጠንቅቀዋል፡፡

ሜዮርካስ በአሁኑ ወቅት በባህር በኩል የሚደረግ የስደተኞች ፍልሰት መጨመሩን የሚያሳይ ምንም ምልክት አለመኖሩንም አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG