እያነጋገሩ ባሉ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ የተጀመረ ተከታታይ ክርክር ነው።
የዕለተ-አርብ እሰጥ አገባ ተከራካሪዎች፤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየታዩ ላሉት ሕዝባዊ ተቃውሞች መንስኤዎችና እንዲሁም በተደጋጋሚ ለሚነሱት የሕዝብ ጥያቄዎች ሁነኛ ምላሽ በየፊናቸው ይቃኛሉ።
ዘለቄታ ባላቸው የፖለቲካ ጥያቄዎችም የመፍትሔ አማራጮች የሚሏቸውን እንደየ-አመለካከታቸው ዝንባሌ በክርክራቸው ይወረውራሉ።
የክርክር ፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የገዢውን ፓርቲ አቋምና ፖሊሲዎች በመደገፍ የቀረቡት አቶ ኤልያስ ግደይ ከአዲስ አበባ፤ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙት ደግሞ አቶ ግዛው ለገሰ ናቸው፤ ከዋሽንግተን ዲሲ።