ቶሮንቶ እና ዴንቨር እና አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሁለት ወገን ክርክር ነው። ሰሞኑን የሆኑትን አነጋጋሪ ጉዳዮች፣ “አሁን ያለንበትን ሁኔታ እና ከፊታችን የሚጠብቀንን ብቻ ሳይሆን፤ እንደ አገር እና እንደ ህዝብ ልናቀና የምንችል እና የሚገባንን” ጥርጊያ ጭምር በሁለት የለየቅል መነጽሮች ለመፈተሽ የሚጥር የእሰጥ አገባ ክርክር ፕሮግራም ነው።
የክርክሩ ተሳታፊዎች አቶ ዮሃንስ አብረሃ ከቶሮንቶ ካናዳ፡ በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት የውጭ አገር ተወካዮች አንዱ ሲሆኑ፤ አቶ ነብዩ አሰፋ ከኮሎራዶ ዩናይትድ ስቴትስ #NoMore መሥራቾች አንዱ ናቸው።
የክርክሩን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።