በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የሳዑዲ አልጋ ወራሽ ‘ጠቅላይ ሚኒስትር’ የሆኑት ክስን ለማምለጥ ነው” ተቺዎች


የሳዑዲ አረቢያ አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን
የሳዑዲ አረቢያ አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን

የሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን በዘውዳዊ ዐዋጅ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግን ያጠለቁት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተለይም በጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ግድያን በተመለከተ ከተመሠረተባቸው ክስ ከልላ ለማግኘት ነው ሲሉ ተቺዎች በመናገር ላይ ናቸው ሲል የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።

የአልጋ ወራሹ አዲስ ተጨማሪ ማዕረግ የታወጀው የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አልጋ ወራሹ ያለመከሰስ መብት ይኖራቸው እንደሁ እየመከረ ባለበት ወቅት ነው።

የአልጋ ወራሹ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ከመታወጁ በፊት አንድ የአሜሪካ ፍ/ቤት ዳኛ ያለመከሰስ መብታቸውን በተመለከተ ከሳሾች የጽሁፍ ጥያቄያቸውን እስከ ዛሬ ሰኞ ድረስ እንዲያቀርቡ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፤ የባይደን አስተዳደር ቢን ሳልማን የያዙትን አዲስ ማዕረግ በመጥቀስ መልስ ለመስጠት የ45 ቀናት ግዜ እንዲሰጠው መጠየቁን ኤኤፍፒ የፍርድ ቤት ሰነዶችን ማየቱን በመጠቀስ ዘግቧል።

ከዓለም ታላቅ የድፍድፍ ነዳጅ አምራች ሃገር ዲፋክቶ መሪ የሆኑት የ37 ዓመቱ አልጋ ወራሽና ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በአሜሪካ በርካታ ክሶች ተከፍቶባቸዋል። ከነዚህም ዋናው በጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ላይ በቱርክ ኢስታንቡል የሃገራቸው ኤምባሲ ውስጥ የተፈፀመውን ግድያ የተመለከተው ነው። በዚህም ለጊዜው ከምዕራቡ ዓለም መገለል ገጥሟቸው ነበር።

“በሳዑዲ አረቢያ የሥልጣን ጫፍ ላይ በመቀመጣቸው ያለመከሰስ መብት ይግባቸዋል” ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል።

የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞችና የመንግሥት ተቺዎች እንደሚሉት ግን፣ አልጋ ወራሹ ጠቅላይ ሚኒስትር መባላቸው፣ ከመከሰስ ነፃ ለመሆንና የሕግ ክለላ ለማግኘት የሚደረግ ዐይን ያወጣ ሙከራ ነው።

XS
SM
MD
LG