በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግሪክ በተዛመተው ቃጠሎ ሰባ አራት ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሃዘን ቀን ታወጀ


ግሪክ ውስጥ በፍጥነት በተዛመተው ቃጠሎ ቢያንስ ሰባ አራት ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በመላ አህገሪቱ የሦስት ቀን የሃዘን ወቅት ታውጇል።

ግሪክ ውስጥ በፍጥነት በተዛመተው ቃጠሎ ቢያንስ ሰባ አራት ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በመላ አህገሪቱ የሦስት ቀን የሃዘን ወቅት ታውጇል። ፈጥኖ ደራሽ ሰራተኞች አሁንም በመኪናዎችና ቤቶች ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ናቸው ብሄራዊ የሃዘን ቀኑን ያወጁት።

ከሁሉም የከፋው ቃጠሎ የደረሰው ራፊና በምትባለው ዋና ከተማ አቴንስ አቅራቢያ የምትገኝ የወደብ ከተማ ሲሆን በርካታ ነዋሪዎች እየሸሹ ወደ ባህር ውሃ ውስጥ ገብተዋል። ጀልባዎች ከሰባት መቶ የሚበልጡ ሰዎችን አውጥተዋል።

ብዙዎቹ ቃጠሎ የደረሰባቸው ወደሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች በሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸዋል። እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቁ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች እንዳሉ ተገልጿል። እጅግ ደረቅ እና ሞቃት በሆነው የአየር ሁኔታ የተነሳውን ቃጠሎ ኃይለኛ ንፋስ ይበልጡን እንዳዛመተው ታውቋል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች አሁንም እሳቱን ለማጥፋት እየተሯሯጡ ናቸው፡፡ ዛሬ በአካባቢው ዝናብ ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG