በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለጸ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ በሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ450 በላይ ቋሚ እና የኮንትራት ቅጥር ሠራተኞች መታሰራቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው እና የፋብሪካው ሠራተኞች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የሱሉላ ፊንጫ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ታዬ፣ ሠራተኞቹ የታሰሩት "በፋብሪካው ይዞታ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የግብርና ሥራ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው፤" ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከፊንጫ ስኳር ፋብሪካ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG