ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ቡድን (ሲፒጄ) ከትናንት በስተያ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ይህንን "በነፃው ፕሬስ ላይ እየተካሄደ ነው" ያለውን የማስፈራራት ዘመቻ አውግዟል፡፡
ሲፒጄ "ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቁጣና ስድብ ተቺ ጋዜጠኝነትን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የተያዘው ዘዴኛ ዘመቻ አካል ነው ብሎ የመንግሥቱ ሚድያ የሚያካሂደው ስም የማጉደፍ ዘመቻ በሃገሪቱ የሠፈነውን የፍርሃት ድባብ ያጠናክራል፡፡ በመሆኑም በዚህ የግሉን መገናኛ ብዙኃን በማዋከብ ዘመቻዋ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ያደርጋት የነበረ ዕድሏን ገደላዋለች" በማለት አስገንዝቧል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡