በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት “ሁሉም ቢተባበር መዘጋጋት አይኖርም” ይላል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዓለም ጤና ድርጅት፣ የኮረና ቫይረሰን ለመከላከል፣ ሰዎች ፈቃደኛ ሆነው፣ ቫይረሱን እንዳይሰራጭ ቢተባበሩና የራሳቸውን እርምጃ ቢወስዱ ኖሮ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የማህበራዊ እንቅስቅሴዎች ገደብ፣ የሥራና የንግድ ተቋማት መዘጋጋትን ማስወገድ ይቻል ነበር ብሏል፡፡ በሌላም በኩልም ሁሉንም ነገር እንደገና ለመዘጋጋት የተወሰነው ውሳኔ፣ በጣልያን ከፍተኛ ቁጣ የቀሰቀሰ ሲሆን በስፔይን ደግሞ በጉዳዩ ላይ መከፋፈል መፈጠሩ ተነግሯል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ሜሪያም ዲያሎ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ፣ “መንግሥት ብቻ ሳይሆን ሰዎችና የንግድ ተቋማትም የኮረና ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ኃላፊነት አለባቸው” ይላል፡፡ የድርጅቱን የኮቪድ 19 ቴክኒክ ጉዳዮች የሚመሩት ማርያ ቫን ከርክሃውስ እንዲህ ይላሉ

“ብሄራዊ ደረጃ ሁሉንም ነገር መዘጋጋቱን ልናስወግደው እንችላለን፡፡ ሁሉም ሰው የበኩሉን ድርሻ ቢወጣ በጅምላ የሚደረገውን የእንቅስቃሴ እገዳን ማስቀረት ይቻላል፡፡ በየእለቱ የህዝብ ክምችት ያለበትን ቦታ ለማስወገድ በየቀኑ የምናስተላልፈው ውሳኔ፣ ለተወሰኑ ጊዜያት በአንዳንድ ቦታዎች የተለየ ገደብና አቀማመጥ እንዲኖራቸው ስናደርግ ወይም አንዳንድ አስፈላጊዎቻችን የሆኑትን ስብሰባዎችንም ሆነ በዓላትን ስንሳተላልፍ፣ እነዚያ የምንክፍላቸው ዋጋዎች ናቸው፡፡”

የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው ፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ የወጣው የኮቪድ 19 ስርጭት መረጃ እንደሚያሳየው 46 ከመቶ የሚሆነው የታየው በአውሮፓ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት፣ የአስቸኳይ ጉዳዮች ድሬክተር ዶ/ር ማይክል ራያን የሚከተለውን ብለዋል፤

“በአሁኑ ሰዓት አውሮፓ ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ያለበት አካባቢ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ብዙ ዝውውርና በነጻነት መቀነሳቀስ ይታያል፡፡ ስለዚህ በሽታውን መላከል በሚጠይቀው መስፈርትና ደንብ መሰረት ወረርሽኙ ያለበትን ሁኔታ በመገንዘብ፣ እንቅስቃሴዎችን መገደብና ሰው ሁሉ በየቤቱ ታቅቦ እንዲቀመጥ ትዕዛዝ መስጠት ያስፈልግ ይሆናል፡፡”

አንዳንዶቹ ግን ተመልሶ ወደ መዘጋጋት መግባቱን አልወደዱትም፡፡ ለምሳሌ ከምሽቱ 11 ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት ድረስ ተግባራዊ በሚደረገው የሰዓት እላፊ ገደቡ ላይ፣ የስፔይን ነዋሪዎች ተከፋፍለዋል፡፡ የአስተዳደር ሠራተኛ የሆኑት፣ ሲሲሊያስለ ሰዐት እላፊው ሲናገሩ

“እርምጃዎቹ በጣም አስፈላጊዎች ነበሩ፡፡ በጣም የከፋ ነገር ስለተደረገ አንድ ነገር መደረግ ነበረበት፡፡” ብለዋል፡፡

በስፔይን ተማሪ የሆነችው አሌክሲያ ደግሞ የተለየ አስተያየት አላት

“ምናልባት የሰዓት እላፊ ገደቡ ለብዙዎች እጅግ የከረረ ሊሆን ይችላል፣ የኢኮኖሚውን ቀውስ ያባባሰውና ሰዎች የበለጠ ኃላፊነት እንዲሰማቸው ሳይሆን ህገ ወጥ የሆኑ ተግባራትን እንዲያደርጉ ሊገፋፋቸው ይችላል፡፡” ብላለች፡፡

ስፔይን በከፍተኛ ደረጃ ከተጎዱ የአውሮፓ አገሮች አንዷ ስትሆን፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጎድተዋል፡፡ ቁጥሩ አሁንም እየጨመረ ነው፡፡ በአገሪቱ ከፍተኛ የቫይረስ ኤክስፐርትና የአስቸኳይ ጤና አስተባባሪው ፈርናንዶ ሲሞን እንዲህ ይላሉ

“እውነታው ቫይረሱ በጣም በቶሎ ነው የሚስፋፋው፡፡ ወደላይ ብቻ ነው እየጨመረ የሚሄደው፡፡ ሁሉንም ነገር በአግባቡ አድርገን፣ የስርጭቱንም ሁኔታም በትትክል አውቀን ካልተቆጣጠርነው በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል፡፡”

በጣልያንም፣ በድጋሚ የተላለፈውን የኮረና ቫይረስ የእንቅስቃሴ ገድብን ጨምሮ የቡናቤቶች ሻይቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 12 ሰዐት እንዲዘጉ የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ ተቆጥተው አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ረጭቷል፡፡ ጣልያን፣ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኮቪድ 19 ተጠቂዎችን ማስመስዘግቧ ተዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት “ሁሉም ቢተባበር መዘጋጋት አይኖርም” ይላል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00


XS
SM
MD
LG