ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ እና የጀርመን ኩባንያዎች ለኮቪድ-19 የመከላከያ ክትባት ፍለጋ በጋራ እያካሄዱ ያሉት የምርምር ሥራ በያዝነው ሳምንት በሰዎች ላይ ሙከራ ወደሚደረግበት የጥናቱ እርከን መሸጋገሩ ይፋ ተደረገ። ከተሳታፊዎቹም አንዳንዶቹም የዩናይትድ ስቴትስ የሕክምና ተማሪዎች ናቸው።
ይህ የአሁኑ ሙከራ የመድሃኒት ኩባያዎች ለኮቪድ-19 ሁነኛ ክትባት ለመፍጠር የሚያስችላቸውን ግኝት ለመቆናጠጥ እሽቅድድም ላይ በሚገኙበት በዓለም ዙሪያ እየተደረጉ ያሉትን ሌሎች መሰል የምርምር ጥናቶች የሚቀላቀል ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።