በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዩናይትድ ኪንግደም ለአፍሪካ የተላኩ የኮቪድ-19 ክትባቶች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ኪንግደም ለአፍሪካ ሃገሮች የላከቻቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች መድረሳቸውን "ጋቪ" በሚል ምህጻረ ቃል የሚጥራው ለክትባቶች ተደራሽነት የሚሰራ ድርጅት አስታወቀ።

ለዛምቢያ 119,200 ለዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ ደግሞ 51ሺሕ 840 የአስትራዜኔካ ክትባቶች በዛሬው ዕለት ይገባሉ ተብሎ መጠበቁን ነው ያስታወቀው።

ኢትዮጵያን፣ ዩጋንዳን እና ኬንያን ጨምሮ ለአሥራ አንድ ሃገሮች ኮቪድ-19ን ለመዋጋት ይችሉ ዘንድ ሃገራቸው የላከችው ሦስት ሚሊዮን ክትባት እየደረሰ ነው ያሉት የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ ይህም በኮቫክስ አማካይነት ልንለግስ ቃል ከገባነው ሰማኒያ ሚሊዮን ክትባት የመጀመሪያው ክፍል ነው ብለዋል።

በኮቫክስ በኩል የሚላከው የመጀመሪያው የብሪታንያው የአስትራዜኔካ ክትባቶች ኢትዮጵያን ጨመሮ ለበርካታ የአፍሪካ ሃገሮች በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ይደርሳል ተብሏል። የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክለውም

"የክትባት እርዳታውን የምናደርገው በዓለም ዙሪያ ሰው ሁሉ ከቫይረሱ ሳይጠበቅ ብቻውን ሊጠበቅ የሚችል ከቶም እንደማይኖር ስለምናወቀው ነው" ብለዋል።

የኢትዮጵያን የክትባት አካሄድ እና የወረርሺኙን ይዞታ ስንመለከት ከጤና ሚስኒቴር ባገኘነው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ እስከትናንት 2302496 ሰዎች ተከትበዋል።

አጠቃላዩ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር 287184 ደርሷል። ከመካከላቸው ከ17,795ቱ በስተቀር የተቀሩት ያገገሙ እንደሆኑ ነው መረጃው የሚያሳየው።

የጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ ሦስተኛ ዙር የሥርጭት ማዕበል መከሰቱን አስታውቆ ጥንቃቄ እንዲደረግ እያሳሰበ ነው። ለቫይረሱ የሚጋለጡት ሰዎችም ለህልፈት የሚዳረጉት እና ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡትም እያሻቀበ መሆኑን አመልክቷል።

ባለፈው ማክሰኞ ለዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ህብረተሰቡ በሙሉ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ በሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ባሁኑ ሰዓት የሚታየው በፍጥነት ተላላፊው ዴልታ የሚባለው የቫይረሱ ዝርያ ይሁን አይሁን ገና በእርግጠኝነት አልታወቀም። ክትትል እያደረግን ነን ብለዋል።

XS
SM
MD
LG