በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን 100 ሚሊዮን ሰዎችን በ60 ቀን ውስጥ ልናስከትብ ነው አሉ


ፕሬዚዳንት ባይደን በትንናትናው እለት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ በዋይት ሐውስ ንግግር ሲያሰሙ
ፕሬዚዳንት ባይደን በትንናትናው እለት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ በዋይት ሐውስ ንግግር ሲያሰሙ

ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት ሀሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሜሪካ ህዝብ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት አብይ ንግግራቸው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መላው አገሪቱን ያሽመደመደበትን አንደኛ ዓመቱን በማሰብ አሜሪካውያን ከፊታቸው የተደቀነውንም ፈተና አብረዋቸው እንዲወጡ እርዳታቸውን ጠይቀዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወርረሽኝ መሆኑን ካስታወቀ አንደኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስካሁን በመላው ዓለም ከ2.6ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲሞቱ በዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ከ530ሺ ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ሁላችንም አንድ ነገር አጥተናል፡፡ የጋራ ስቃይ የጋራ መ ስዋዕትነት፣ በሰዎች ህይወት መጥፋት እና ሁላችንም ህይወታችንን የተቀማንበት ዓመት ነበር፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ 50 ቀናት በኋላ ትናንት ሀሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ባስተላለፉት አብይ ንግግራቸው አስተዳደራቸው ወረርሽኙኝ ለማስወገድ ያለውን ዝርዝር እቅድ ይፋ አድርገዋል፡፡ በአንድ መቶ ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን ሰዎች ለማስከተብ ያስቀመጡት እቅድ ከታሰበው በላይ መሄዱንም ተናግረዋል፡፡
በእርግጥ ለነገሩ በአስተዳደሬ የመጀመሪያዎቹ መቶ ቀናት ውስጥ፣ 100 ሚሊዮን ሰዎችን እናስከትባለን በማለት ያስቀመጥነውን ግብ፣ በ60ዎቹ ቀናት ውስጥ ለመድረስ እየተቃረብን ነው፡፡ የትኛውም አገር ይህንን አላደረገም፡፡
ባይደን ሁሉም ክፍለ ግዛቶች ክትባቱን መውሰድ የሚችሉትን ሁሉንም አሜሪካውያን እስከ ግንቦት ወር መጀመሪያ እንዲያስከተቡ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በርካታ መሰናክሎችም ተደቅኖባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ አሜሪካውያን ክትባቱን ለመውሰድ እያንገራገሩ ሲሆን እንደ አንዳንድ የክልል መንግሥታትም የፌደራል መንግሥቱን የጤና ደንቦችና ትዕዛዝትን መከተል አይፈልጉም፡፡ ለምሳሌ በቴክሳስ የፊትና የአፍንጫ ጭምብል የማድረጉ አስገዳጅነት እንዲቀር ተደርጓል፡፡
የፊትና አፍንጫ መሸፈኛውን ጭንብል ማጥለቅ ህይወት ለማዳን ከሚደረጉ ነገሮች ውስጥ አነስተኛው ነው፡፡ ይህ አንዳንዴ ሊከፋፍለን ይችላል፤ ክፍለ ግዛቶች ከክፍለ ግዛቶች ግን አብረው ተባብረው እንደመስራት እርስበርሳቸው ይናቆራሉ፡፡
ተንታኞች እንደሚሉት በክትባቱ እና በጤና ደንቦች ላይ ፖለቲካዊ ልዩነቶች ጥላቸውን አጥልተዋል፡፡ በተለይ ወረርሽኙ ገና በተከሰበታቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ላይ ልዩነቶቹ እጅግ የጎሉ ነበሩ፡፡
በቺካጎ ዩኒቨርስቲ፣ የህዝብ ፖሊሲ የሀሪስ ትምህርት ቤት ዲን የሆኑት ካትሪን ቤከር እንዲህ ይላሉ
ሰዎች ስለ ህዝብ ጤና የተምታቱ መልእክቶችን እየሰሙ ነው፡፡ የፖለቲካ ሁኔታው በጣም ጫፍና ጫፍ ሆኗል፡፡ ስለዚህ በህዝቡ ዘንድ ጤናን አስመልከቶ በሳይንስ ላይ ያለው ጥርጣሬ ለህዝብ የሚተላለፉ የጤና መልዕክቶችን ጎድቷቸዋል፡፡ በርግጥ ሰዎች ከሚሰሟቸው የተምታታቱ መል ዕክቶች አንጻር ተንስተው መሆኑ ይገባኛል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ነገር ዘላቂ ጉዳት ከሚያስከትሉ ነገሮች አንዱ ይመስለኛል፡፡
ትናንት ጧት ላይ ባይደን የ 1.9 ትሪሊዮን ዶላር የተመደበለትን የኮረና ቫይረስ የእፎይታ ህግ ፈርመዋል፡፡ ኢኮኖሚውንም ለማነቃቃት ጭምር ሲባል በህግ አውጭዎቹ ምክር ቤቶች የወጣው ይህ ህግ ከሪፐብሊካን አባላት የአንዳቸውንም ድጋፍ አላገኘም፡፡

ባይደን 100 ሚሊዮን ሰዎችን በ60 ቀን ውስጥ ልናስከትብ ነው አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00


በተወካዮቹ ምክር ቤት የሪፐብሊካን መሪ የሆኑት ኬቪን መካርቲ ምክንያቱን እንዲግ በማለት ያስረዳሉ
ይህ ህግ፣ የነፍስ አድን ህግ አይደለም፡፡ ገንዘቡም የእርዳታ ሂሳብ አይደለም፡፡ ይልቁንስ የግራ አክራሪዎች ከወረረሽኙ በፊት ያቀረቡት የወጪ ዝርዝር ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን የኮቪድ 19 የእፎይታ ህግ የሚሰጠውን ጥቅም ለአሜሪካ ህዝብ ለማስረዳት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች “እርዳታው ይኸውላችሁ” በሚል የጉዞ ፕሮግራም የሚያደርጉ መሆኑም ተዘግቧል፡፡
የዋይት ሀውስ የቪኦኤ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክሱዋራ ካጠናቀረቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

ባይደን 100 ሚሊዮን ሰዎችን በ60 ቀን ውስጥ ልናስከትብ ነው አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

XS
SM
MD
LG