በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 ማስክ መመሪያ ፈተና ገጥሞታል


ፎቶ ፋይል፦በኒው ዮርክ
ፎቶ ፋይል፦በኒው ዮርክ

የባይደን አስተዳደር የፍሎሪዳው ፌዴራል ፍርድ ቤት በህዝብ መገናኛ ቡዙሃን ተጠቃሚዎች ላይ የተላለፈው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) መመሪያ ተግባራዊነትእንዲቀር ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ፍትህ ሚኒስቴርና የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) መመሪያው ለህዝብ ጤና ወሳኝ በመሆኑ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ የአየር መንገድ ተጓዦች የማስክ አጠቃቀም ውሳኔውን አስመልክቶ የተለያየ አመለካከት ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በርካታ አየር መንገዶችና አውሮፕላን ማረፊያዎችም፣ በተለይ እንደ ዳላስ አትላንታ ሎስ አንጀለስን ሶልት ሌክ ሲቲ የመሳሰሉት የማስክ መመሪያውን ለሰዎች ምርጫ ትተዋል፡፡

እንደ ኒው ዮርክ፣ ቺካጎ፣ ሎስ አንጀለስና ኬኔትኬት የመሳሰሉት አሁንም ማስክ ማድረግን እንደሚያስገድዱተነገሯል፡፡ የተቀሩት ግን የሲዲስ መመሪያው እንዳለ ቢሆንም መመሪያውን እስናካቴው ተግባራዊ እንደማያደርጉት ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG