በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒት ማመርቻ አስመረቀች


 ፓትሪክ ሱን ሺሆንግ እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳት ሲሪል ራማፎሳ
ፓትሪክ ሱን ሺሆንግ እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳት ሲሪል ራማፎሳ

ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒት ማምረቻ ፋብሪካ በትናንትናው እለት መርቃ ከፍታለች፡፡

ፋብሪካውን መርቀው የከፈቱት የደቡብ አፍሪካው ተወላጅ ቢሊዮኔር ፓትሪክ ሱን ሺሆንግ እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳት ሲሪል ራማፎሳ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

መራቂዎቹ በወቅቱ ባሰሙት ንግግር ፋብሪካው አፍሪካ ውስጥ የሚመረት የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 መድሃኒት ብቻ ሳይሆን የካንሰር ክትባቶችንና ሌሎች መድሃኒቶችን እንደሚያመርት መናገራቸውን ከኬፕታወን የደረሰን የቪኦኤ ሪፖተር ቪኪ ስታርክ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ፋብሪካውን ለማጠናቀቅ 196 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣና እስከ ሚቀጥለው ዓመት 2025 ድረስ 1 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒቶችን እንደሚያመርት ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG