ዋሺንግተን ዲሲ —
ደቡብ አፍሪካ የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመቆጣጠር ስትል፣ ለሦስት ወራት ያህል ተዘግታ ከቆየች በኋላ፣ በቅርቡ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ፣ ምግብ ቤቶችና ካዚኖዎች ወይም የቁማር ቦታዎችን፣ መክፈት እንደምትጀመር ታውቋል።
የሃገሪቱ ፕረዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ትናንት ማታ በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር፣ ፍቃድ ያላቸው ማረፍያ ቤቶችና የውበት ቦታዎችም እንደሚከፈቱ ተናግረዋል።
አንዳንድ ዕገዳውችን ለማላላት የተወሰነው፣ ጥብቅ ቫይረሱን የመከላከል ተግባር ስለሚፈጸምበት ሁኔታ፣ ከኢንዱስትሪ ተወካዮችና ከሳይንስ ምሁራን እንዲሁም ከአካባቢ መንግሥታዊ መሪዎች ጋር፣ ውይይት ከተደርገ በኋላ መሆኑን ራማፎሳ ጠቁመዋል።
ፕረዚዳንቱ አክለውም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንባል ማድረግን የመሳስሉ፣ የኮሮናቫይረስ መዛመትን ለመቅነስ የሚችሉ ተግባሮች የሚከበሩ ከሆነ፣ ሲኔማ ቤቶችን ያካተቱ የበዙ የንግድ ተቋማትም ይከፈታሉ ብልዋል።
ደቡብ አፍሪካ ከ80,000 በላይ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንዳልዋት፣ ከ1,600 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደሞቱባት አስታውቃለች።