በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከፋይዘር ኩባንያ የኮቪድ-19 መድሃኒት ለመግዛት ንግግር ላይ ነች ተባለ


የኮቪድ-19 መድሃኒት
የኮቪድ-19 መድሃኒት

ዩናይትድ ስቴትስ ከፋይዘር ኩባኒያ ጋር በሙከራ ላይ ከሚገኘው የኮቪድ-19 መድሃኒቱ ለአስር ሚሊዮን ህሙማን ህክምና የሚበቃ ልትገዛ ድርድር ይዛለች ተባለ።

በዘገባዎች መሰረት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፋይዘር ኩባንያ እያደረገበት ያለውን ፀረ ቫይረስ መድሃኒት ለመግዛት አምስት ቢሊዮን ዶላር ለመመደብ ማቀዳቸውን ነው የተዘገበው።

ዘገባው የወጣው ፋይዘር ጄኔቫ ከሚገኘው በተመድ የሚደገፈው ሜዲሲን ፓተንት ግሩፕ የተባለ የህዝብ ጤና ጥበቃ ቡድን ጋር በአቅም ተመጣጣኝ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች መድሃኒቱን ለዘጠና አምስት ሃገሮች እንዲያመርቱ ፈቃድ ለመስጠት ሥምምነት በተፈራረመ ማግስት ነው።

በተደረሰው ሥምምንት መሰረት መድሃኒቱ ከዓለም ህዝብ ሃምሳ ሦስት ከመቶው ለሚኖርባቸው ባለዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ሃገሮች ተደራሽ ይሆናል።

ፓክስሎቪድ የተባለው መድሃኒት በኮቪድ-19 ከባድ ባልሆነ ደረጃ የታመሙ ሰዎችን ህመማቸው ሆስፒታል መግባት ወይም ሲከፋም ለህልፈት በሚያደርስ ደረጃ እንዳይጸና በዘጠና ከመቶ እንደሚከላከል ፋይዘር አመልክቷል። ነጻ የመድሃኒት ጉዳይ ኤክስፐርቶችም መድሃኒቱ ከወዲሁ አበረታች ውጤት እያሳየ በመሆኑ ፋይዘር የቀጠለው ቀጣይ ጥናት እንዲቋረጥ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።

XS
SM
MD
LG