ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት እኤአ በተያዘው የ2021 የተመዘገበው የኮቪድ-19 ሟቾችና ተጋላጮች ቁጥር ከላፈው የ2020 የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ግምት ተናገሩ፡፡
ባለሥልጣናቱ ምንም እንኳ የኅዳርና ታህሳስ ወር ቁጥሮች ለብዙ ሳምንታት የማይታወቁ ቢሆንም እሳካሁን ባሉት መረጃዎች በ2021 የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ቢያንስ በ15ሺ ሊበልጥ እንደሚችል ገምተዋል፡፡
ይህ አሃዝ ከዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል /ሲዲሲ/ የተገኘ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ያለፈው ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ከፍተኛ ሰዎች የሞቱበት ሲሆን አብዛኛው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሲዲሲ ትናንት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ከ3.3 ሚሊዮን በላይ ሰው የሞተበት የአውሮፓ 2020ው ከተባለውም የከፋ ሲሆን ቀደም ሲል ሪፖርት ከተደረገው በላይ 25ሺ ሰዎች የሞቱበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ሲዲሲ በዩናይትድ ስቴትስ 65 ከመቶ ወይም 240 ሚሊዮን አሜሪካውያን ሙሉ ክትባት የወሰዱ መሆናቸውን ሲገልጽ ቀሪዎቹ አሁንም ለመከተብ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተገልጿል፡፡