በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህሙማን የሕክምና ቀጠሯቸውን እንዳያራዝሙ እንደሚሻ የብሪታንያ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ


የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለንደን የሚገኘው ሚልተን ኬይንስ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በጎበኙበት ወቅት
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለንደን የሚገኘው ሚልተን ኬይንስ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በጎበኙበት ወቅት

በኮቪድ-19 ሳቢያ ሌሎች የህክምና ቀጠሮዎቻቸውን ያዘገዩ ሰዎች ወደ ብሄራዊው የጤና አገልግሎት ተቋም መጥተው እንዲታከሙ የሚፈልጉ መሆናቸውን የብሪታኒያው የጤና ሚኒስትር ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ሳጂድ ዣቪድ ለስካይ ኒውስ በሰጡት በዚህ አስተያየታቸው “ሁሉም ህሙማን እንዲመጡ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ተቋማችን ተዘጋጅቶ የሚጠብቃቸው መሆኑን እንዲረዱ ስለምሻ” ነበር ያሉት።

ዣቪድ አክለውም ቁጥራቸው ከ8 እስከ 9 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የተቋሙ ሰራተኞች የኮቪድ-19 ታማሚዎችን በመርዳት ተጠምደው ስለነበር “ባሉበት እንዲቆዩ” ተጠይቀው እንደነበር አስታወሰው፤ አሁን ግን ብሄራዊው የጤና አገልግሎት እንዲጠባበቁ አቆይቷቸው የነበሩትን ሕሙማን ለመርዳት ዝግጁ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG