በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲዲሲ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች 3ኛው የሞደርናና ፋይዘር ክትባት ይረዳል አለ


የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ
የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ ትናንት ሀሙስ ባወጣው መግለጫ የሰውነት የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆነ ሰዎች ሦስተኛው የፋይዘር ወይም የሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ወደ ሆስፒታል የመግባታቸውን አስፈላጊነት በእጅጉ እንደሚቀንሰው አስታወቀ፡፡

ሲዲሲ በመግለጫው የሰውነት የመቋቋም አቅማቸው ደካማ በሆኑ ሰዎች ላይ በተደረገው ጥናት የማጠናከሪያው ሳይሆን ሦስተኛው ዙር ክትባት ወደ ሆስፒታል የመግባትን አስፈላጊነት 88 ከመቶ የሚቀንሰው መሆኑን አመልክቷል፡፡

መንግሥት ባለፈው ነሀሴ የሰውነት ወይም የተፈጥሮ የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች ሦስተኛውን የፋይዘር ወይም የሞደርና ክትባት መስጠት እንደሚቻል መፍቀዱ ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG