በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ፎቶ ፋይል፦

በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ዛሬ ከአስር ሚሊዮን እያለፈ ነው። ወረርሺኙ ከገባ ጀምሮ ባልታየ መልኩ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ባለፈው ሳምንት በየቀኑ በአማካይ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የቫይረሱ ተያዦች የተገኙ ሲሆን በንፅፅር ይህ አሃዝ ባለፈው ወር በዚሁ ጊዜ ከነበረው ዕጥፍ መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም በየቀኑ ቁጥራቸው ወደ ዘጠኝ መቶ የሚደርስ ሰዎች ህይወታቸው አልፉል። ማዕከላዊ ምዕራብ ክፍለ ግዛቶቿ በብዛት የተጠቁት ሲሆን ሆስፒታል የሚገቡ ህሙማን ቁጥር ከምንጊዜውም ጨምሯል።

አዲስ ተመራጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በመጪው ጥር ወር አስተዳደሩን ሲረከቡ ወረርሺኙን ለመዋጋት ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ማቀድ ይዘዋል። ዛሬ የኮሮናቫይረስ ግብረ ሃይል ስብሰባ ያካሂዳሉ፤ በመቀጠልም “ወረርሽኙን የምናሸንፈበት ዕቅድ” ያሉትን የሚዘርዝር ንግግር ያደርጋሉ።

በሌላ በኩል የአሁኑን አስተዳደር የኮቪድ ምላሽ የሚመሩት ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ እአአ ከጥቅምት 20 ቀን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የግብረ ሃይሉን ስብሰባ ያካሂዳሉ።

ኮቪድ-19 በተቀረውም የዓለም አካባቢ አውሮፓን ጨምሮ በከባዱ ጨምሮ እየተዛመተ ነው።

በአውሮፓ በርካታ ሃገሮች የቫይረሱን መዛመት ለመግታት የተለያዩ የእንቅስቃሴ መዝጋት ርምጃዎች ወስደዋል። በዓለም ዙሪያ የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር ከሃምሳ ሚሊዮን አልፏል። አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG