በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዚላንድ የኮቪድ-19 ክትባት ተቃውሞ ወደ ረብሻ ተቀየረ


በኒው ዚላንድ የኮቪድ-19 ክትባት መመሪያን በመቃወም ሰልፈኞች ድንኳኖችን፣ ፍራሾችን እና ወንበሮችን አቃጥለዋል፤ እአአ መጋቢት 2/2022
በኒው ዚላንድ የኮቪድ-19 ክትባት መመሪያን በመቃወም ሰልፈኞች ድንኳኖችን፣ ፍራሾችን እና ወንበሮችን አቃጥለዋል፤ እአአ መጋቢት 2/2022

በኒው ዚላንድ የኮቪድ-19 ክትባት መመሪያን በመቃወም በመቀመጥ ሲያምጹ የነበሩ ሰዎችን ለማስነሳት ፖሊስ የጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ረበሻ ተቀይሯል፡፡ ዌሊንግተን በሚገነኘው ፓርላማ ውስጥ ትናንሽ መጠለያዎችን ይዘው ተቀምጠው የቆዩት ተቃዋሚዎች መጠለያዎቹ ላይ እሳት የለቀቁ ሲሆን ፖሊስ እሳቱን ለማጥፋት ሲጥር ታይቷል፡፡ እሳቱ ተሰፋፍቶም ከዓመት በፊት የተከፈተ የሕጻናት መጫወቻ ቦታን አጋይቷል፡፡

ተቃዋሚዎቹ የውሃ ኮዳዎችን እና ሌሎች እቃዎችን በፖሊሶች ላይ እየወረወሩ ከአካባቢው የሸሹ ሲሆን ሦስት የፖሊስ አባላትም እምብዛም ያልከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በፖሊሶች እና በተቃዋሚዎች መሃከል ዛሬ ጠዋት ግጭቱ የተጀመረው ፖሊሶች የድምፅ ማጉሊያ በመጠቀም ተቃዋሚዎቹ የተከለከ ቦታ ላይ በመሆናቸው ለቀው እንዲወጡ በጠየቁበት ሰዓት ላይ ነው፡፡ በመቀጠልም ፖሊሶቹ አስለቃሽ የበርበሬ ጭሶችን የረጩ ሲሆን ሰልፈኞቹም በዓይናቸው ላይ ወተት ሲያፈሱ ነበር፡፡ በዚህ ግጭት ፖሊስ በትንሹ 60 ሰዎችን አስሯል፡፡

የኒው ዚላንድ ዋሺንግተን ተቃውሞ በካናዳ ኦቶዋ ግዛት የተደረገውን ዓይነት ተመሳሳይ ተቃውሞ የተደረገ ሲሆን ላለፉት ሦስት ሳምንታት ቆይቷል፡፡ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ተቃዋሚዎቹ “በሃሰተኛ መረጃ እና የሴራ ሃሳቦች በመታለል የኮቪድ-19 አሰራጮች ሆነዋል” ብለዋል፡፡

ኒው ዚላንድ እስካሁን ድረስ የኮቪድ-19 ተጠቂዎችን እና 56 ሞቶችን ማስተናገዷን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል አስታውቋል፡፡ ይህም ሊሳካ የቻለው የጠቅላይ ሚኒስተር አርደን አስተዳደር ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ በማስቀመጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይሁንና 5 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ሃገሪቱ በቅርብ ሳምንታት ከባድ የሆነ የኦሚክሮን ግርሽ የተመዘገበባብት ሲሆን ከሦስት ቀናት በፊት በእንደ ቀን ብቻ 32,674 የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ተገኝተውባታል፡፡

XS
SM
MD
LG