በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
“የባይደን አስተዳደር የክትባት ግዴታ መመሪያ እርምጃ ትክክለኛ ነው” - ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

“የባይደን አስተዳደር የክትባት ግዴታ መመሪያ እርምጃ ትክክለኛ ነው” - ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ


ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ፎቶ ፋይል፦ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት መከተብ ግዴታ የሚያደርገውን የባይደን አስተዳደር መመሪያ "የግል ነጻነት መጣስ ነው" የሚለውን የወግ አጥባቂዎች ክርክር የፕሬዚዳንት ባይደን የጤና አማካሪ አንተኒ ፋውቺ ውድቅ አደርገውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዋና የጤና ጉዳዮች አማካሪ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ የአስተዳደሩን የክትባት ግዴታ መመሪያዎች ትክክለኛ ነው ሲሉ ተሟግተዋል።

ፋውቺ ትናንት ዕሁድ በፎክስ ቴሌቪዢን ቀርበው በሰጡት ቃለ መጠይቅ ክትባት ግዴታ ማድረግ የሰዎች የራሳቸውን የጤና ጉዳይ የመቆጣጠር ነጻነትን መጣስ ነው በሚል ከወግ አጥባቂ ሪፖብሊካን የክፍለ ሀገር አስተዳዳሪዎች በኩል የሚቀርበውን ሙግት አጣጥለዋል።

የህዝብ ጤና ጥበቃ ቀውስ ሲከሰት እና ያልተለመደ ሁኔታ ሲደቀን ያልተለመደ እርምጃ ይጠይቃል፥ እንደ አሁኑ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እና ክትባት ትዕዛዝ ማለት ነው ሲሉ አስረድተዋል። አስከትለውም "ይህ እርምጃ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም እንደግለሰብ የምንኖረው በራሳችን ዓለም ታጥረን አይደለም፥ ህብረተሰብ ውስጥ ነው" ያሉት ፋውቺ ህብረተሰብ ደግሞ ጥበቃ ከበሽታ መጠበቅ አለበት፥ ይህ የሚከናወነውም ራስን ብቻ በመጠበቅ ሳይሆን ተከትቦ የሌሎችንም ጤና በመጠበቅ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ ከአንድ መቶ በላይ ሰራተኞች ያላቸው ድርጅቶች ክትባቱን መውሰድ አለዚያ በተደጋጋሚ የቫይረሱን ምርመራ ማድረግ ግዴታ እንዲያደርጉ መመሪያ የሰጡ ሲሆን መመሪያው ተግባራዊ የሚሆነው ከሁለት ሳምንታት በኋላ ነው።

የሃገሪቱ የጦር ኃይል አባላት እና የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞችም እንዲከተቡ መመሪያ መሰጠቱ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG