በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ የምራቅ ምርመራ ጸደቀ


ኮሮናቫይረስ በምራቅ ሲመረመር
ኮሮናቫይረስ በምራቅ ሲመረመር

ጥናቱ የተካሄደው በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ክፍል ሲሆን ገና በሌሎች የሙያው ምሁራን እንዳልተገመገመ ተገልጿል።

የአሜሪካው የል ዪኒቨርሲቲ ያፈለቀውን የኮቭድ 19 ቫረስን በምራቅ የመመርመሩ ዘዴ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት እጥቅም ላይ እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ትላንት አጸደቀው።

በምራቅ የሚደረገው ምርመራ ከ 24 ሰአታት ባነሰ ፍጥነት ውጤቱ ሊገኝ እንደሚችል ዋጋውም ርካሽ እንደሆነ ወደ $10 ዶላር ገደማ መሆኑ ተገልጿል።

አዲሱ የምርመራ ዘዴ የፀደቀው አንዳንድ የፌደራልና የጤና ባለስልጣኖች በሀገሪቱ የቫይርሱ ምርመራ እንዲበራከት እየጠየቁ ቢሆንም በየቀኑ የሚደረግ የቫይረሱ ምርመራ እንደቀነሰ በተገለጸነት ወቅት ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 ህሙማንና በሙታኑ ብዛት ከአለም ቀዳሚ ቦታ መያዝዋ በቀጠለበት ወቅት ነው ይህ የሆነው።

በአለም ደረጃ የኮቪድ 19 በሽተኞች ብዛት እስከ ዛሬ ንጋት በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ 21 ሚሊዮን በላይ መሆኑን ስለጉዳዩ የሚከታተለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዪኒቨሲቲ አስታውቋል። ከ5.3 ሚልዮን በላይ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ3.3 ሚልዮን ደግሞ በብራዚል መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው አሀዝ አመልክቷል።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት ህንድ ከ 2.5 ሚልዮን በላይ በኮቪድ የተያዙ በሽተኞች አሏት። ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች በሞት ተለይተዋል።

XS
SM
MD
LG