በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአለም ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ስዎች ከ 15.7 ሚልዮን በላይ ደረሱ


የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትላንት የብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፖሬሽን BBC ባደርገላቸው ቃለ-መጠይቅ ሲናገሩ ኮሮና ቫይረስ በገባባቸው የመጀመርያ ጥቂት ሳምንታትና ወራት ውስጥ ቫይረሱ ምን ያህል ውስብስብ እንደሆነ መንግስታቸው አልተረዳም ነበር ብለዋል።

ምናልባትም ከመጀመርያውኑ ያላየነው ነገር ቢኖር ቫይረሱ የህመም ስሜት ከሌለባቸው ሰዎች ሊተላለፍ የሚችል መሆኑን ነው በማለትም አስገንዝበዋል። የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት ብሪታንያ ወደ 300,000 የሚጠጉ የቫይረሱ በሽተኞች አልዋት። በሞት የተለዩት ደግሞ ወደ 46,000 እንደሚጠጉ ታውቋል።

አለም አቀፉ ቫይረስ በሚዛመትበት በአሁኑ ወቅት የምናደርገው ሁሉና የምንውላቸው ስዎች ሳይቀር “የሞትና ሂወት ጉዳይ ሆኗል” ሲሉ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አኪይጅ ዶክታር ቴድሮስ አድሀኖም አሳስበዋል።

“የናንተ ሂወት ባይሆንም እንኳን ለምትወድዋቸው ስዎች ወይም ለማታውቋቸውም ቢሆን “የሞትና የሽረት” ጉዳይ ሊሆን ይችላል በማለትም ዶክተር ቴድሮስ አክለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ዶክተር ቴድሮስ በቻይና ተገዝተው በኮሮናቫይረስ ለደረሰው ሞት ምክንያት ሆነዋል ሲሉ በያዝነው ሳምንት ለተናገሩት ዋናው የጤና ድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ምላሽ ስጥተዋል።

“የአለም የጤና ድርጅት በእንደዚህ አይነት አነጋገር ከስራው አይዛነፍም። የአለም ማህበረሰብም እንዲዛንፍ አንሻም” የተደቀነብን ትልቁ አደጋ አለም አቀፉን ወረርሽኝ የፖለቲካ ገጽታ እንዲኖረው የማድረጉ ተግባር መቀጠል ነው” የሚል ምላሽ ስጥተዋል ዶክተር ቴድሮስ። ፖለቲካና ወገንተኝነት ሁኔታዎችን አባብሰዋል ሲሉም አክለዋል።

በአለም አቀፍ ደርጃ በ 24 ሰአታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር በ 284,196 ማደጉን የሚሞቱት ስዎች ብዛት ደግሞ በ 9,753 ከፍ ማለቱን አለም አቀፍ የጤና ድርጅት አስታውቋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ በሽተኞች ብዛት ከአለም ቀዳሚ ቦታ መያዙን ቀጥላለች። በአሁኑ ወቅት 4.1 ሚልዮን ደርሰዋል። ሁለተኛዋ ብራዚል ስትሆን 2.2 ሚልዮን የቫይረሱ በሽተኞች አልዋት። ህንድ ደግሞ 1.3 ሚልዮን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስዎች እንዳልዋት በአለም ዙርያ ስለኮሮና ቫይረስ ሁኔታ የሚከታተለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዪኒቨርሲቲ ጠቁሟ።

በአለም ደርጃ15.7 ሚልዮን በኮሮናቫይረስ የተያዙ ስዎች እንዳሉ በሞት የተለዩት ከ 639,000 በላይ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG