በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ መዛመት ሽቅብ እየወጣ መሆኑ ተገለጸ


ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የኮሮንቫይረስ መዛመት በአንዳንድ የአለም ክፍሎች ሽቅብ መውጣቱ እንደቀጠለ ታውቋል።

የኮሮናቫይረስን ጉዳያ የሚከታተለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት በአሁኑ ውቅት በአለም ዙርያ ከ 12.7 ሚልዮን በላይ የኮቪድ 19 በሽተኞች አሉ። የሞቱት ደግሞ ከ 3.2 ሚልዮን በላይ ናቸው።

ዩናይተድ ስቴት ውስጥ ከ 3.2 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ከ 134,000 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን እንዳጡ ታውቋል።

የዩንይትድስ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመርያ ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርገው በታዩበት ትላንት ዕለት ብቻ 66,528 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተገልጿል። ፕረዚዳንቱ ጭምብል ያደረጉት ዋልተር ሪድ በተባለው ብሄራዊ ወታደራዊ ሆስፒታል በሄዱበት ወቅት ነው።

ትራምፕ የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመካላከል ሲሉ ጭምብል በሚያደርጉ ጋዜጠኞችና ሌሎች ሰዎች ላይ ሲያፌዙ ቆይተዋል።

አንዲት አባታቸው በቫይረሱ ተይዘው የሞቱባቸው ሴት “ግልጽ የሆነ የአመራር ብቃት አላሳዩም ያልዋቸውን የአሜሪካ ባለስልጣኖች ለአባታቸው ሞት ተጠያቂ ማድረጋቸውን The Arizona Republic የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

የአሜሪካ ፖለቲከኞች የኮሮናቫይረሱ መዛመት ክብደትን ለመቀበል ባለመፈለግ አደጋውን ለማቅለል የሚያስችሉ ወሳኝ መመርያዎችን ለማውጣት ባለመቻልና ፍልጎት ባለማሳየት የአመራር ጉድለት አሳይተዋል በማለት መንቀፋቸውን ጋዜጣው ጠቁሟል።

ደቡብ ካሮላይና ትላንት ከ 2,200 በላይ አዲስ የቫይረሱ በሸታኞች መገኘታቸውን አስታውቃለች። ሉዊዝያና ደግሞ ባለፈው አርብ ከ 2,600 በላይ አዲስ የቫይረሱ በሽተኖች እንዳሉ ባለፈው አርብ ገልጻለች።

የኮሮናቫይረስ በሽታን ሲያጣጥሉ የቆዩት የብራዚል ፕረዚዳንት ጄየር ቦልሶናሮ በቫይረሱ እንደታያዙ ባለፈው ማክሰኞ ከተገለጸ ወዲህ ተለይቶ መቆየት ከጀመሩ የመጀርያውን ሳምንት ተይይዘውታል። ለወራት ያህል ሲያፌዙበት የቆዩትን የአፍና አፍንጫ ጭንብል ማድረግና የአካል ርቀት መጠበቅ መመርያን መከተል ግድ ሆኖባቸዋል።

ባለቤቸውና ሁለት ሴት ልጆቻቸው ተመርምረው ከባይረሱ በሽታ ነጻ መሆናቸውን የፕረዚዳንቱ ባለቤት ትላንት ተናግረዋል።

ሜክሲኮ ትላንት ከ 6,000 በላይ አዲስ የኮቪድ 19 በሽተኞች ማግኘትዋን

ገልጻለች። ሩስያም ከ 6,000 በላይ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች እንዳሏት ዛሬ ጠቁማለች።

በጃፓን መዲና ቶክዮ ዛሬ 206 አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች እንደተገኙ ሀገሪቱ አሳውቃለች። ጃፓን ውስጥ ለተከታታይ አራት ቀናት ከ 200 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ስዎችን ስታገኝ ቆይታለች።

XS
SM
MD
LG