በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው ተቃውሞ የወረርሽኙን መዛመት ሊያባብስ እንደሚችል ተገለጸ


የኒውዮርኩ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ።
የኒውዮርኩ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ።

የጆርጅ  ፍሎዪድን  ሞት  በመቃወም  አሜሪካ  ውስጥ  እየተካሄደ  ባለው  ህዝባዊ  ተቃውሞ  ምክንያት፣ የኮሮናቫየስ  በአዲስ  መልክ ሊዛመት  ይችላል  ሲሉ  የዩናይትድ  ስቴተስ  የጤና  ጥበቃ  ባለስልጣኖች  እያስጠነቀቁ ነው። ዝርዝር ዘገባው ቀጥሎ ይቀርባል።

የጆርጅ ፍሎዪድን ሞት በመቃወም አሜሪካ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት የኮሮናቫየስ በአዲስ መልክ ሊዛመት ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ስቴተስ የጤና ጥበቃ ባለስልጣኖች እያስጠነቀቁ ነው።

አፍሪቃቂው አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒሶታ ከተማ ላይ የሞተው ፖሊሶች መሬት ላይ አጋድመውት እጁ በካቴና ታስሮ አያለ አንድ ነጭ ፖሊስ ጉልበቱን አንገቱ ላይ ተጭኖበት ለዘጠኝ ደቂቃዎች ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ከቆየ በሁዋላ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ይህን ድርጊት በመቃወምም አሜሪካውያን በሀገሪቱ ዙርያ ድምጻቸውን በሚያሰሙበት በአሁኑ ወቅት አፋቸውንና አፍንጫቸውን በጭንብል የሸፈኑ ሰዎች ቢኖሩባቸውም ያልሸፈኑም ይታያሉ። በተቃውሞ ወቅት የአካል መራራቅ ለመተግበርም አይቻልም።

የሚኒሶታ ክፍለ-ግዛት አስተዳደሪ ቲም ዋልዝ ለአሶሼተድ ፕረስ የዜና አገልግሎት ሲናገሩ ወረርሺኝ ባለበት ወቅት መሆናችንን ደጋግሜ ማስታወሱን አቀጥላለሁ ብለዋል። አሁንም ሀኪም ቤቶቻችን በኮቪድ 19 በሽተኞች ተሞልተዋል ሲሉም አክለዋል።

የአትላንታ ከንቲባ ኬይሻ ላንስም በተለይም ጥቁሮችና ቡናማ ሰዎች በብዛት የሚሞቱበት ወረርሽኝ ላይ ነን ያለነው በማልት ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ከ 1.7 ሚልዮን በላይ የኮቪድ 19 በሽተኞች ያሉ ሲሆን ከአለም ቀዳሚ ቦታ ይዛለች። ከ 100,000 በላይ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

በአለም ደረጃ፣ የቫይረሱ መዛመት እየተስፋፍ ሄዶ የቫይረሱ በሽተኞች ብዛት ከ 6 ሚልዮን ባላይ መድረሱ ታውቋል።

ብራዚል ወደ 500,000 የሚጠጉ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች ያልዋት ሲሆን ከአለም ሁለተኛዋ ሆናለች። የጤና ጥበቃ ባለስልጣኖች እንደሚሉት ላቲን አሜሪካ በኮሮናቫይረስ መዛመት ቀጣይዋ ማእከል ልትሆን ትችላለች።

የሰው ልጆችና የኮሮና ቫይረስ ግንኙነት እድሜ ልክ ሊሆን ይችላል ሲሉ የተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሀውስ ለብሪታንያው ዘጋርዲያን ጋዜጣ ተናግረዋል። ፕሮፌሰሩ የሚያስተምሩት ኤደንበርግ ዪኒቨርሲቲ ላይ ነው።

የክትባት መድሀኒት ካልተገኘና የአካል መራራቁ ጉዳይ ካልተተገበረ በስተቀር ለበሁተኛ ዙር በርትቶ ሊከሰት የሚችለው ወረርሺኝ አደገኛ ይሆናል በማለት ፕሮፌሰሩ አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG