በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አስተዳደሩ የማጠናከሪያ ክትባቱን እቅድ ውድቅ አደረገ


የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር (FDA)
የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር (FDA)

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር (FDA)የመንግስት ክትባት አማካሪ ቡድን ፣ ሶስተኛውን የማጠናክሪያ ክትባት "ለሁሉም ሰው" እንዲሰጥ የቀረበውን እቅድ በትናንትናው እለት 16 ለ 2 በሆነ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ይህ ለሁሉም አሜሪካውያን በሚባል ደረጃ ፣ተጫማሪ ክትባት ለመስጠት ተችሎት ለነበረው የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር፣ ትልቅ ፈተና ይሆንበታል ተብሏል፡፡

ዋይት ሀውስ፣ ባለፈው ወር፣ የፋይዘር ወይም የሞደርና ክትባቶችን የወሰዱ፣ ሁሉም አሜሪካውያን፣ ሁለተኛውን ዙር ክትባቶቻቸውን ከወሰዱበት 8 ወር በኋላ፣ ተጨማሪውን የማጠናከሪያ ክትባት መውሰድ ይችላሉ ብሎ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ፣ ለሁሉም አሜሪካውያን እንዲሰጥ የታሰበውን የማጠናከሪያ ክትባት ውድቅ ያደረገው የምግብና መድሃኒት አስተዳደሩ፣ የክትባት አማካሪ ቡድን፣ እድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑ ሰዎችና፣ በተለያዩ በሽታዎች ተጋልጠው፣ ከፍተኛ የጤንነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ግን፣ ማጠናከሪያውን መውሰድ ይችላሉ ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG