በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልጆች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አንዳለባቸው ተገለፀ


የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም
የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም

የኮሮናቫይረስን መዛመት ለመቆጣጠር ሲባል ከ12 ዓመት እድሜ በላይ የሆኑት ልጆች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አንዳለቸው ከስድስት እስከ 11 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ልጆች ደግሞ እንደአስፋላጊነቱ ጭምብል እንዲያደርጉ ዓለምአቀፍ የጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት መመርያ አውጥቷል።

ተለቅ ያሉት ልጆች ከትንንሾቹ ይልቅ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ሁለቱ ድርጅቶች አስገንዝበዋል። ሁሉም ልጆች ምን ያህል ቫይረሱን ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ለመረዳት ገና ጥናት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ሁለቱ ድርጅቶች ገልጸዋል።

ከአምስት ዓመት እድሜ በታች የሆኑት ልጆች ጭምብል ማደረግ አያስፈልጋቸውም ብለዋል የዓለም የጤና ድርጅትና የህጻናት መርጃ ድርጅት።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት በዓለም ደረጃ በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ብዛት ከ23 ሚልዮን በላይ ደርሷል። ለህልፈት የተዳረጉት ደግሞ ትናንት 800,000 ደፍነዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ከ5.6 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ከ176,000 በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG