በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ ክትባት


እንግሊዝ አሜሪካዊው የመድኃኒት ምርምርና አምራች ኩባንያ ፋይዘር የሠራው ክትባት ለአጣዳፊ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውል ፈቀደች።

የሃገሪቱ የመድኃኒቶችና የጤና ጥበቃ ምርቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ከጀርመኑ ባዮንቴክ ጋር በመተባበር እየሠራ ያለው የፋይዘርን ክትባት አገልግሎች እንዲውል ዛሬ ፍቃድ መስጠቱ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መድኃኒትን በመጠቀም እንግሊዝን ከምዕራቡ ዓለም የመጀመሪያ ያደርጋታል።

ክትባቱ በሚቀጥለው ሣምንት መሰጠት የሚጀምር ሲሆን የብሄራዊው የጤና አገልግሎች ባልደረቦች እንዲሁም የአረጋዊያን መጦርያ ቤቶች ነዋሪዎችና ሠራተኞች የመጀመሪያዎቹ ተከታቢዎች እንደሚሆኑ ታውቋል።

በዓለም ዙሪያ ወደ 64 ሚሊየን የሚሆን ሰው ለኮሮናቫይረስ መጋለጡንና ወደ አንድ ሚሊየን ተኩል የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሰው በኮቪድ 19 መሞቱን በየዕለቱ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

XS
SM
MD
LG