በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 መጠናከሪያ ክትባት ከ18 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ እንዲፈቀድ ተጠየቀ


በዩናይትድ ስቴትስ 18 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ሰዎች በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት ማጠናከሪያውን መውሰድ እንዲፈቀድ መጠየቁን ፋይዘር ኩባኒያ አስታወቀ።

የመድሃኒት ኩባኒያው በጉዳዩ ዙሪያ የተካሄደ አዲስ ጥናት ሪፖርት ጠቅሶ ትናንት ማክሰኞ ለዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ጥያቄውን አቅርቧል።

በሁለት ጊዜ የሚሰጠውን የፋይዘሩን ክትባት ሦስተኛ ማጠናከሪያውን የወሰዱ አስር ሽህ በጎ ፈቃደኞች ያሳተፈ ጥናት መካሄዱን ፋይዘር ገልጾ በክትትሉ የመጀመሪያ ውጤት መሰረት ሦስተኛውን ማጠናከሪያ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቫይረሱን በዘጠና አምስት ከመቶ የሚከላከል መሆኑ እንዳሳየ ጠቅሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር እና የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ ማጠናከሪያ ክትባቱን መውስደ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ከጥቂት ሳምንታት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ከስድሳ አምስት ዓመት በላይ የሆኑ እና ቫይረሱ ቢይዛቸው በጠና የመታመም አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም የጤና ሰራተኞችን ጨምሮ የስራቸው ጸባይ ለቫይረሱ በጣም የሚያጋልጣቸው ሰራተኞች በሙሉ ማጠናከሪያ ክትባት እንዲከተቡ ፈቅደዋል።

ፋይዘር የመጀመሪያውን ክትባታቸው የእርሱን ሳይሆን የሞደርናውንም ሆነ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰኑን ክትባት ለወሰዱ ሰዎችም ጭምር ማጠናከሪያውን ክትባት አቅርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብሪታንያ እና የስዊድኑ የመድሃኒት ኩባኒያ አስትራ ዜኔካ ሙሉ በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባቶች እና መድሃኒቶችን የሚሰራና የሚያመርት ክፍል ሊያቋቁም መሆኑን አስታወቀ።

በሌላ ዜና ደግሞ ጀርመን ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።

ይህንኑ ተከትሎም የበርሊን ከተማ ቻሪቴ ሆስፒታል በቫይረስ ተላላፊ በስታዎች ኃላፊዋ ዶክተር ክሪስቲያን ድሮስተን የክትባት ሂደቱ ካልተፋጠነ አንድ መቶ ሺህ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ በዛሬው እለት አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG