በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 ያስጨነቀው ዓለም


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዓለም ከአሮጌው 2020 ዓ.ም ወደ አዲሱ 2021 ዓ.ም ሲሻገር 84 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 ተጋልጠዋል 1.8 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አጥተዋል።

አዲሱ የአውሮፓውያን 2021 በገባበት በዚህ ወቅት፣ በመላው ዓለም 84 ሚሊዮን ሰዎች ለኮቪድ 19 መጋለጣቸውን 1 .8 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሕይወታቸው ማለፉን የጆንስ ሀፕኪንስ የኮሮና ቫይረስ የመረጃ ማዕከል በዕለታዊ መረጃው አስታወቀ።

20 ሚሊዮን ሕዝቦቿ በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት እና 345 ሺሕ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት ዩናይትድ ስቴትስ ከየትኛው ስቴትስ የዓለም ክፍል ከፍ ያለው ቁጥር የተመዘገበባት አገር ሆናለች። እንደ ጆን ሀፕኪንስ ገለጻ ህንድ ለቫይረሱ የተጋለጡ 10.2 ሚሊዮን ሰዎች አሏት። 148 ሺሕ ሰዎች በወረርሽኑ ህይወታቸውን በማጣታቸው ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች፡፡ 7.7 ሚሊዮን ሰዎች በመያዛቸው ደግሞ ብራዚል ሦስተኛ ደረጃ ላይትገኛለች።

የብሪታኒያ የጤና ባለሥልጣናት የመጀመሪያው ዙር ወረርሽኝ ሲመጣ የተገነቡ የድንገተኛ ሕመምተኛ መቀበያ ሆስፒታሎችን እንደገና በመክፈት ላይ ይገኛሉ። አገሪቱ ይበልጥ ተስፋፊ የሆነውን አዲሱን ቫይረስ ለመዋጋት በመታገል ላይ ትገኛለች።

የብሪታኒያ የጤናማዕከል ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ለንደን ውስጥ የሚገኘው ናይትኒጌል ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ለቫይረሱ ተያዦች ተከፍቶ የነበረውን ክፍል እንደገና ለመክፈት እያዘጋጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። ናይትኒጌል በከተማው ዙሪያ ለመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እንዲያገለግል በወታደሮች የተገነባ ሲሆን እስከ አሁን ደግሞ መጠባበቂያ ሆኖ ቆይቷል።

በብሪታኒያ ትላንት አርብ አርብ 55 ሺህ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተያዦችን መዝግባለች። የጤና ባለስልጣናቱ ይህ ቁጥር የአዲሱ ቫይረስ ውጤት እንደሆነ ይናገራሉ። አዲሱ ቫይረስ በ33 አገራት ውስጥ መታየቱን ዘግቧል። ወደ 40 የሚጠጉ አገራት ደግሞ ከብሪታኒያ የሚደረግማንኛውንም ጉዞ ላይ እቀባ ጥለዋል።

ቱርክ 15 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተያዦችን ከመዘገበች በኋላ ቫይረሱ የመጣው ከብሪታኒያ መሆንን በመግለፅ የጉዞ ገደብ አስቀምጣለች። በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ውስጥ ከኮሎራዶና ከካሊፎርኒያ ቀጥሎ ሦስተኛውን በአዲሱ ቫይረስ የተያዘ ሰው መዝግባለች። ፈረንሳይ 2.6 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ስለተያዙባት ከደቡብ አውሮፓ ቀዳሚ አገር ሆናለች። ለዚህም ይመስላል 100 ሺሕ ወታደረችን አሰማርታ የአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል እንዳይከበር ስትቆጠጠር የዋለችው።

የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በግዙፉ የአሜሪካ መድሃኒት አምራች ኩባኒያ ፋይዘርና የጀረመኑ ኩባንያ ባዮቴክ የበለፀገውን የፀረ ኮቪድ 19 ክትባት ለአጣዳፊ ችግሮች መጠቀም የሚቻል መሆኑን በመፍቅድ በማደግ ላይየሚገኙ አገሮች ክትባቱን በቶሎ የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸቱን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ክትባቱን የሙቀቱ መጠን ከ70 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች በሆኑ ማቀዝቀዣ ቦታዎች ማስቀመጥን፣ በብርቱ ጥንቃቄ ማጓጓዝና ስርጭቱንም ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አቅምንየሚጠይቅ በመሆኑ ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡

የቻይና ባለስልጣናት የቻይና መድሃኒት አምራቾች ላበለፀጉትና ለአገሪቱ የመጀመሪያ ለሆነው የኮቪድ ክትባት ፈቃድ ሰጠ። የመንግሥቱ ብሔራዊ የመድሃኒት ምርቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ዛሬ ሐሙስ ይፋ እንዳደረገው፤ በመንግስቱ ሲኖፋርም ለተያዘው የቤጂንግ የመድሃኒት አምራች ኢንሲቲዩት ፍቃድ የተሰጠው ክትባቱ 79.3 በመቶ ቫይረሱን የመቋቋም አቅም እንዳለው ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የውጭ ባለሞያዎች ሲኖፋርም ላይ ጥያቄ እያስነሱ ይገኛሉ። ምክኒያቱም ክትባቱ በገለልተኛ አካል ሊረጋገጥ የሚያስችለውን አስፈላጊ መረጃዎች አላቀረበም ብለውታል።

አዲሱ ፍቃድ የተሰጠውና አምስት ኩባንያዎች ያመረቱት የቻይናው ክትባት አሁንም ለሶስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ቢሆንም እስካህን 4.5 ሚሊዮን ሰዎች እንዲከተቡት ተደርጓል።

አስትራዚንካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በጋራ በመተባበር ያበለፀጉት የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ብሪታንያ ፈቃዷን የሰጠችው አዲሱ ክትባትም በብዛት መታዘዘ ጀመሯል።

የፋይዘር ባዮቴክ ክትባትን ጨምሮ ኮቪድ-19ኝን ለመዋጋት በመመረት ላይ ያሉት ክትባቶች ኮሮናቫይረስ ወደ 1.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት በመላው ዓለም በቀጠፈበት በዚህ የ2020 ማጠናቀቂያ ወቅት መልካም ዜና ናቸው ተብለዋል።

በሌላ በኩል የካሊፎርኒያ የጤና ባለስልጣናት በብሪታኒያ የታየው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ በካሊፎርኒያ በአንድ ሰው ላይ መታየቱን አስታውቀዋል ምናልባትም በሌሎች ሰዎች ላይ ሳይኖር አይቀርም ሲሉ ጥርጣሬያቸውን አጋርተዋል። አዲሱ ቫይረስ በዩናይትድስቴትስ ሲታይ ባለፈው ሳምንት በኮሎራዶ ከታየው ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።

XS
SM
MD
LG