በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ኮቪድ የዓለምን የነፍስ ወከፍ እድሜ አሳጥሯል"


የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባላፈው ዓመት የነበረውን የዓለምን የነፍስ ወከፍ እድሜ አሳጥሯል ሲል በዚህ ሳምንት የወጣ አንድ ዓለም አቀፍ ጥናት አመለከተ፡፡

በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የህብረተሰብ ጤና ፕሮፌሰር ናዙር ኢስላም የሚመራው የአጥኚዎች ቡድን ከዚህ ድምዳሜ የደረሰው በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛና መከላከኛ ገቢ ባላቸው 37 አገሮች እኤአ ከ2005 እስከ 2019 የሞቱትን ሰዎች የነፍስ ወከፍ እድሜ ላይ ባደረገው ጥናት መሰረት ነው፡፡

ቢኤምጄ በተባለው የሳይንስ መጽሄት ላይ የወጣው ዘገባ የነፍስ ወከፍ እድሜ በከፍተኛ ደረጃ የወደቀው በሩሲያ መሆኑን ገልጾ የወንዶች በ2.33 የሴቶች ደግሞ በ1.14 ዓመት መቀነሱን አመልክቷል፡፡

ከሩሲያ ቀጥሎ ሁለተኛ የዩናይትድ ስቴትስ በወንዶች 2.27 ሴቶች ደግሞ 1.61 ዓመት መቀነሱን የአጥኚዎቹ ቡድን ግኝት አስታውቋል፡፡

በድምሩ 31 የሚሆኑ አገሮች የነፍስ ወከፍ እድሜያቸው የቀነሰባቸው ሲሆን ጨምሮ የተገኘባቸው ወይም ምንም ለውጥ ያልታየባቸው አገሮች ስድስት ብቻ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል፡፡

የተጠቀሱት ስድስቱ አገሮች ዴንማርክ፣ አይስላንድ፣ ኒው ዘላንድ፣ ኖርዌይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ታይዋን ናቸው፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን በመላው ዓለም ከ5 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በወረርሽኙ መሞታቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG