በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዘው ሰው ቁጥር እየጨመረ ነው


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

በአፍሪካ ሃገሮች የጸረ ኮቪድ-19 ክትባት ሂደት ዝግተኝነት እና ኮሮናቫይረሱ የሚያዘው ሰው ብዛት እየጨመረ መሆኑ የአህጉሪቱን የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት አሳስቧል።

አፍሪካ ከዓለም ህዝብ አስራ ስምንት ከመቶውን የሚይዘው አንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ህዝብ ያላት ሆኖ ሳለ በዓለም ዙሪያ ሥራ ከዋለው የክትባት መጠን ውስጥ የደረሳት ሁለት ከመቶው ብቻ መሆኑን አሶሼየትድ ፕሬስ ዘግቧል፤ እስካሁን አንድም ሰው ያልተከተባቸው የአፍሪካ ሃገሮች አሉ።

ሃገሮች እስከመጪው መስከረም ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከህዝባቸው አስር ከመቶውን እንዲያስከትቡ የዓለም የጤና ድርጅት ያወጣውን ግብ ዘጠና ከመቶው የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገሮች እንደማያሳኩ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG