በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማላዊ ውስጥ ኮሮናቫይረስ ማገርሸቱ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማላዊ ውስጥ አግርሽቷል
ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማላዊ ውስጥ አግርሽቷል

ማላዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማገርሽቱ ከባድ ችግር ላይ እንዳለች ተገለጸ። በቫይረሱ ሳቢያ የታመሙ ዜጎችን ህይወት ለማትረፍ በተያዘው ርብርብ የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት እና ዋናው ስቴዲየም ወደሆስፒታልነት ተቀይሯል።

አስተዳደሩን ከያዙ ገና መንፈቃቸው የሆነው የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛረስ ቻክዌራ በዚሁ በጥር ወር ውስጥ ሁለት ሚኒስትሮቻቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ሞተውባቸዋል፥ ሁኔታው በፈጠረው ድንጋጤም በርከት ያሉ የቫይረሱን መከላከያ መመሪያዎች እየወጡ ናቸው።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መጀመሪያ የተቀሰቀሰው በይበልጥ ተላላፊው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ደካማ የጤና ጥበቃ ስርዓት ያላት ማላዊም መግባቱ ተረጋግጧል።

XS
SM
MD
LG