በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዴክሳሜታዞን ካለሃኪም ትዕዛዝ አትውሰዱ" የጤና ሚኒስቴር ማሳሰቢያ

Dr. Lia Tadesse, Minister of Health of Ethiopia, speaks during an urgent press conference at the Federal Ministry of Health after the first case of COVID-19 coronavirus was detected in Ethiopia, in Addis Ababa, March 13, 2020.

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ 399 ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጡ መገኘታቸውን የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 መድረሱን ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

194 ወንዶች እና 204 ሴቶች ሲሆኑ 398ቱ ኢትዮጵያውያን እና 1 የውጭ ሃገር ዜጋ ናቸው፡፡ 135 ሰዎች ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ፣ 132 ከደዎሊና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ፣ 86 ከአዲስ አበባ፣ 18 ከአማራ፣ 14 ሰዎች ከድሬዳዋ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 1 ሰው ሶማሌ ክልል፣ 2 ከትግራይ፣ 1 ከድቡብ ክልል፣ 1 ሰው መሆናቸውን መረጃው ዘርዝሯል

ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት 82 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ፣ 2 ከሶማሌ፣ 1 ከትግራይ፣ 1 ከኦሮሚያ እና 1 ሰው ከጋምቤላ በድምሩ 95 ሰዎች ከቫይረሱ እንዳገገሙ አክሎ ገልጿል

በሌላ በኩል የጤና ሚኒስቴሩ ዴክሳሜታዞን በቅርቡ ለጽኑ ሕሙማን መተንፈሻ ማገዣነት ባለው ጠቃሚነት የተነሳ በድንገተኛ ክፍል ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኑን አስታውሶ ነገር ግን መድሃኒቱ ኮቪድ 19ን ለመካላከል እንደማይጠቅም እና የጎንዮሽ ጉዳት የሚያመጣ በመሆኑ ያለ ሃኪም ትዕዛዝም መወሰድ እንዳሌለበት በማሳሰብ መድሃኒት መደብሮችም ያለሃኪም ማዘዣ መድሃኒቶቹን ከመሸጥ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

XS
SM
MD
LG