በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢዮጵያ ውስጥ ዛሬ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሃኪሞች አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ የህክምና ማእከል የኮቪድ 19 በሽተኞች ላይ የመተንፈስ መሳርያን እንዴት እንደሚጠቀሙ ሲሰለጥኑ።
የኢትዮጵያ ሃኪሞች አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ የህክምና ማእከል የኮቪድ 19 በሽተኞች ላይ የመተንፈስ መሳርያን እንዴት እንደሚጠቀሙ ሲሰለጥኑ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2836 የላብራቶሪ ምርመራ መቶ ዘጠኝ (109) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ቫይረሱ የተገኝባቸው ሰዎች ከ5 ዓመት እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 61 ወንዶች እና 48 ሴቶች ናቸው፡፡

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2836 የላብራቶሪ ምርመራ መቶ ዘጠኝ (109) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ቫይረሱ የተገኝባቸው ሰዎች ከ5 ዓመት እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 61 ወንዶች እና 48 ሴቶች ናቸው፡፡

99 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ከትግራይ፣ 5 ከኦሮሚያ እና 3 ሰዎች ከሃረሪ ክልል መሆናቸውን የጤና ሚኒስተር ዛሬ ከሰዓት በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ ከነዚህ ውስጥም 94 ቱ ምንም ዓይነት ንክኪም ሆነ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፣ 2 ሰዎች የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እንዲሁም 13 ሰዎች የታወቀ ንክኪ የነበራቸው ናቸው፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ሁለት(1172) ደርሷል፡፡ በትላንትናው ዕለት የ3 ኢትዮጵያውያን ህይወት ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ ከኮሮና ጋር በተያያዘ እስካሁን ባለው ጊዜ 11 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል:: በሌላ በኩል አንድ(1) ሰው ከትግራይ ክልል ያገገመ ሲሆን በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 209 ነው፡፡

XS
SM
MD
LG