በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ኮቪድ 19 እየተባባሰ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት የደረሰው የህይወት ጉዳት 1706 መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ የኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል የዛሬን መረጃ ሳይጨምር ሦስት መቶ ሰዎች የፅኑ ህመም ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

እስከዛሬ ምርመራ ከተደረገላቸው ከአንድ ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ በላይ ከሚሆኑ ሰዎች 110 ሺህ ሰባ አራቱ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው መረጋገጡን ዶ/ር ተገኔ አመልክተው ሰዉ ‘አስገዳጅ መመሪያ ተነስቷል፤ ኮሮናቫይረስ የለም’ በሚሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እየተመራ እራሱን እያጋለጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ አስገዳጅ መመሪያውም አለመነሳቱን፣ የቫይረሱ ሥርጭትም እየተባባሰ መሆኑን ዶ/ር ተገኔ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG