በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በሮሒንግያ ሥደተኞች መጠለያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ባንግላዲሽ በሚገኘው ግዙፉ የሮሒንግያ ሥደተኞች መጠለያ ካምፕ አንድ ስደተኛ እና አንድ የአካባቢው ነዋሪ ላይ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘ ተዘግቧል። የዓለም የጤና ድርጅት በፍጥነት ክትትል የሚያደርግ ቡድን እንደተሰማራ አስታውቋል። ከሁለቱ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሌሎች ሰዎችን ፣ መከታተል ተጀምሯል ብሏል። ሁለቱም ለይቶ ማቆያ እንደገቡም ተጠቁሟል። በባንግላዲሽ የህጻናት አድን ገብረ ሰናይ ድርጅት ተጠሪ እንደተናገሩት ቫይረሱ ግዙፉ የስደተኛ ካምፕ መግባቱ፣ ብዙ ሺህ ሰው እንደሚሞት በርግጠኝነት መናገር ይቻላል ብለዋል።

ሀገሪቱንም በአሥርታት ወደኋላ ሊመልሳት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል። ግዙፉ የስደተኛ ክምፕ ከገባ ካምፑ ንጽህና የጎደለው መሆኑ በፍጥነት ሊዛመት እንደሚችል የእርዳታ ድርጅቶች ቀደም ብለው ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

XS
SM
MD
LG