በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም በኮቪድ-19 የሞተው ሰው ብዛት ከ5 ሚሊዮን አለፈ


የሕክምና ባለሞያዎች በሪቪን ፣ ዩክሬን ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሞተውን ታካሚ አስከሬን ሲያጓጉዙ
የሕክምና ባለሞያዎች በሪቪን ፣ ዩክሬን ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሞተውን ታካሚ አስከሬን ሲያጓጉዙ

በዓለም ላይ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊዮን መድረሱን የጆን ሀፕኪንስ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ዛሬ ማለዳ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

5 ሚሊዮን 425 ሆኖ የተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር ባለፈው ሰኔ 4 ሚሊዮን ከነበረው ቁጥር በአንድ ሚሊዮን የጨመረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ይህ ቁጥር የተመዘገበው አንዳንድ አገሮች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እንኳን ለማግኘት በሚታገሉበትና ሌሎች ደግሞ የማጠናከሪያ ክትባት ለመስጠት በሚዘጋጁበት ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትም ጉባኤያቸውን በማድረግ ለሚገኙት የቡድን 20 አገሮች በድሆቹና በበለጸጉ አገሮች መካከል ያለው የክትባት ስርጭት ልዩነት አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል፡፡

ድርጅቱ ፣ ወረርሽን መቋቋም የሚቻልበት ብቸኛ መንገድ ለሁሉም ሰው ፍትሃዊና የተቀናጀ የማህብረሰብ ጤና ተደራሽነት ሲኖር ብቻ መሆኑን ታሪክና ሳይንስ የሚያስረዳ መሆኑን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG