በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ዜናዎች


የጆን ሆፕኪንስ የኮሮናቫይረስ የመረጃ ማዕከል በዓለም ላይ 238 ሚሊዮን ሰዎች ለኮቪድ-19 የተጋለጡ ሲሆን ወደ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ መሞታቸውን ዛሬ ማለዳው ላይ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

እስካሁን በመላው ዓለም 6.5 ቢሊዮን የክትባት መድሃኒቶች መሰራጨታቸውንም ማዕከሉ አመልክቷል፡፡

በዚህ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በአገሪቱ የሚገኘውን ሁሉንም ነገር ክፍት ያደረገችው ኒው ዚላንድ በ“ዘመናዊ የዘር ማጥፋት” ልትጠየቅ ትችላለች ሲሉ የአገሬው ሰዎች ወይም (indigenous people) የሆኑት የማኦሪ ፖለቲከኞች አስጠነቀቁ፡፡ መከፈቱን ተከትሎ በአገሪቱ ባላፈው ቅዳሜና እሁድ 95 የቫይረሱ ተጋላጮች የተመዘገቡ ሲሆን ዛሬ ሰኞም 35 አዲስ ተጋላጮች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

ለቫይረሱ ከተጋለጡትም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአገሬው ሰዎች ማሆናቸውን ፖለቲከኞቹ አስታውቀዋል፡፡

የብራዚል ፕሬዚዳን ጃሪ ቦልሶኖራ ትንናት እሁድ በኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ሳቢያ ከአገሪቱ ሳንቶስ ከተማ ከሚደረገው የእግር ኳስ ሻምፒዮን ጨዋታ ውድድር ተመልካችነት አልተከትብክም ተብዬ መታገዴ አበሳጭቶኛል አሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ያልተከተቡ ሲሆን የኮረና ቫይረስን ወረረሽኝ በማናናቅ የሚታወቁ ናቸው፡፡

የጆን ሀፐኪንስ የኮረና ቫይረስ የመረጃ ማዕከል አማካይነት በብራዚል እስካሁን ለኮረና ቫይረስ የተጋለጡ ከ21 ሚሊዮንን በላይ ሰዎች ሲሆኑ 600 ሺ የሚሆኑት ደግሞ በወረርሽኙ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG