በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትልቋ የቻይና ከተማ ሻንግሃይ የኮቪድ ቁጥጥሩ እየጠበቀ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ቤጅንግ፣ ቻይና
ፎቶ ፋይል፦ ቤጅንግ፣ ቻይና

የኮሮናቫይረስ አዲስ ተጋላጮች ቁጥር መደዳውን እየቀነሰ ቢሆንም የቻይና ሻንግሃይ ከተማ ባለሥልጣናት በ26 ሚሊዮኑ የከተማዋ ነዋሪ ላይ የእንቅስቃሴ ገደቡን ይበልጡን አጥብቀዋል።

የአንዳንዶቹ ሰፈሮች ነዋሪዎች ለሦስት ቀናት ያህል ከቤት እንዳይወጡ እና ከውጭ ቁሳቁስ እንዳይቀበሉ በፅሁፍ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ነዋሪዎች ወጥተው እንዲዘዋወሩ ተፈቅዶ ስለነበር በአዲሱ መመሪያ ግር ብሏቸዋል። ከዚህም ሌላ የሻንግሃይ ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ የተያዘ ጎረቤት ያላቸው ሰዎች ከቤታቸው በግድ ወደሆቴል ወይም ወደማቆያ ማዕከል እየተወሰዱ ነው የሚሉ ሪፖርቶች በማኅበራዊ መገናኛዎች ላይ ወጥተዋል።

ሙሉ የመከላከያ አልባሳት የለበሱ አጽጂ ሰራተኞች በየመኖሪያ ቤት እየገቡ ተሃዋሲ ማጥፊያ እየረጩ መሆናቸውም ተገልጿል።

አንድ የከተማዋ ባለሥልጣን ለአሶሲየትድ ፕረስ በሰጡት ቃል የጋራ ማዕድ ቤቶች እና መፀዳጃ ቤቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ጸረ ተሃዋሲ መድሃኒት የመርጨት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዋና ከተማዋ በቤጅንግም ባለሥልጣናት የእንቅስቃሴ ገደቦቹን እያጠበቁ ሲሆን የጅምላ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ቀጥሏል። ተጨማሪ ጎዳናዎች ተዘግተዋል።

XS
SM
MD
LG