በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ የኮሮናቫይረስ የምርመራ ዘዴ በአፍሪካ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

አዲስ፣ ፈጣን ውጤት የሚገኝበት የኮሮናቫይረስ የምርምራ ዘዴ፣ በቅርቡ በመላ አፍሪካ ተደራሽ እንደሚሆን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። በአህጉሪቱ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ድርጅቱ ጠቁሟል።

አዲሱ ያነሰ ዋጋ የሚከፈልበት የምርመራ ዘዴ፣ የጤና ስርዓቶች በኮሮናቫይረስ የታመሙ ሰዎችን በፍጥነት አግኝተው ለማከም እንደሚረዳቸው፣ በአፍሪካ የዓለም የጤና ድርጅት ቀጠናዊ ሥራ አስኪያጅ ማችሺዲሶ ሞየቲ አስገንዝበዋል።

20ሚሊዮን የሚሆኑ የምርመራ መሳርያዎች፣ ዝቀተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ሃገሮች፣ እየተከፋፈሉ መሆናችውን ብዙ ደግሞ ወደ አፍሪካ ማምራታቸውን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣኗ ጠቁሟል።

“ይህ ቫይረሱን ለመታግል በሚደረገው ጥረት፣ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። እንዲህ ዓይነቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው የምርመራ መሳርያ፣ አፍሪካ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራ አስፈላጊነትን ያሟላል” ብለዋል ሞየቲ።

አሁን የሚገኘው አዲስ የምርመራ መሳርያ፣ እስካሁን ባለው ጊዜ የሚሰራበት፣ የላብራቶሪ ምርመራ ሂደት አያስፈልገውም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG